በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢንዶኔዥያ በደረሰ የአጥፍቶ ጠፊ ፍንዳታ በትንሹ 10 ሰዎች ቆሰሉ


በኢንዶኔዥያዋ ሱራባያ ከተማ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢስ ጣቢያ ላይ የደረሰ የአጥፍቶ ጠፊ ፍንዳታ፣ በትንሹ 10 ሰዎችን ማቁሰሉ ተገለፀ።

በኢንዶኔዥያዋ ሱራባያ ከተማ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢስ ጣቢያ ላይ የደረሰ የአጥፍቶ ጠፊ ፍንዳታ፣ በትንሹ 10 ሰዎችን ማቁሰሉ ተገለፀ።

ከአንድ ቀን ቀደም ብሎ በዚያችው ከተማ ውስጥ በሚገኙ 3 አብያተ ክርስቲያናት ላይ 3 የተቀነባበሩ የአጥፍቶ ጠፊ ፍንዳታዎች መድረሳቸውም ታውቋል።
ሁለቱም ፍንዳታዎች የተካሄዱት በቤተሰብ በተደራጁ አጥቂዎች ሲሆን፣ የቤተ ክርስቲያናቱን ያካሄዱት፣ ሁሉም መሞታቸው በተረጋገጠው በ6 የቤተሰብ አባላት ሲሆን፣ ፖሊስ ጣቢያው ላይ የደረሰው ደግሞ፣ አንዲት የ8 ዓመት ዕድሜ ያላት ግን በሕይወት የተረፈች ልጅ ባለችበት በ5 የቤተሰብ አባላት መሆኑ ታውቋል። አንዲት ሴትና ህፃናት በዚህ በአብያተ ክርስቲያናቱ ጥቃት ተሳታፊዎች ሲሆኑ ይህ የመጀመሪያው እንደሆነም ተመልክቷል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG