በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢንዶኔዢያ ምርጫ 200 ሚሊዮን ሰዎች ድምፅ ሰጡ


ነዋሪዎች በምርጫ ጣቢያ ደርሰው ድምጽ እየሰጡ ቦጎር፣ ምዕራብ ጃቫ፣ ኢንዶኔዥያ እአአ የካቲት 14/2024
ነዋሪዎች በምርጫ ጣቢያ ደርሰው ድምጽ እየሰጡ ቦጎር፣ ምዕራብ ጃቫ፣ ኢንዶኔዥያ እአአ የካቲት 14/2024

በኢንዶኔዢያ ዛሬ ረቡዕ በተደረገ ፕሬዝደንታዊ እና የምክር ቤት አባላት ምርጫ 200 ሚሊዮን ሰዎች ድምፅ እንደሰጡ ሲዘገብ፣ በአንድ ቀን ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ድምፅ ሰጪዎች የተሳተፉበት ምርጫ ሆኖ ተመዝግቧል።

በሶስት የሰዓት ዞኖች በምትከፈለውና 17 ሺሕ ደሴቶች ባላት አገር የተደረገው ምርጫ ቆጠራ መጀመሩም ተዘግቧል።

ሁለት የአምስት ዓመታት የሥልጣን ዘመን ያጠናቀቁትን ፕሬዝደንት ጆኮ ዊዶዶን ማን የተካል የሚለው ጥያቄ፣ የመራጮችን ትኩረት የሳበ ነው ተብሏል።

“ምርጫው ዲሞክራሲን የምናከብርበት በዓል ነው። በአቀኝነት፣ በግልጽ እና በነፃ እንደሚካሄድ ተስፋ አለኝ” ሲሉ ተደምጠዋል ተሰናባቹ ፕሬዝደንት፡፡

ሕዝቡ በምርጫው እንደሚያሸንፉ ተስፋ የጣለው፣ ባለፉት ሁለት ምርጫዎች በዊዶዶ የተረቱት የ72 ዓመቱ የመከላከያ ሚኒስትር ፕራቦዎ ሱቢያንቶ ላይ እንደሆነ በመነገር ላይ ነው። ሱቢያንቶ የዊዶዶን ልጅ በምክትል ፕሬዝደንትነት አጭተዋል። የወቅቱን ፕሬዝደንት ዊዶዶን ተወዳጅነት ለመጠቀም የተዘየደ እንደሆነ ተዘግቧል።

የድምጽ ቆጠራውና የውጤት እወጃው ሳምንታትን ሊወስድ እንደሚችል ታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG