በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ህንድ በተቀሰቀሰ ግጭት ወታደሮቿ መገደላቸውን ገለጸች


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ህንድ በምታስተዳድረው የካሽሚር አካባቢ ከነውጠኞች ጋር በተቀሰቀሰ ግጭት ሦስት የመንግሥቱ ወታደሮች መገደላቸውን አስታወቀች። ትናንት አምስት ወታደሮቿ፣ ተገድለውባታል።
ግጭቱ የተቀሰቀሰው ህንድ በቅርቡ ባካሄደችው የማጥቃት ዕርምጃ ሀያ ሁለት ታጠቂዎች ከገደለች በኋላ ነው፤ በዚያ ግጭት ሀያ ወታደሮቼ ተገድለውብኛል ስትል ኒውዴልሂ ተናግራለች።
ባለፈው ዓመት የካቲት ወር ላይ ነውጠኞቹ ባደረሱት አጥፍቶ ጠፊ ጥቃት፣ አርባ ፖሊሶች ከገደሉባት ወዲህ ይህ ከፍተኛው ቁጥር መሆኑ ነው። ህንድ ታጣቂዎቹን በገንዘብ ትደግፋለች ብላ ፓኪስታንን ትወነጅላለች፣ ኢስላማባድ ታስተባብላለች።

XS
SM
MD
LG