በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ህንድ በፓኪስታን ላይ የአየር ጥቃት እንደምታደርስ ገለፀች


ፓኪስታን ውስጥ በሚገኝ ጃኢስ ኢ ሞሀመድ የሚባል እስላማዊ ታጣቂ ቡድን ካምፕ ላይ ንጋት ላይ የአየር ጥቃቶች አደርሳለሁ ስትል ህንድ አስታወቀች።

ፅንፈኛው ቡድን ከሁለት ሳምንታት በፊት ህንድ ካስሚር ግዛት ውስጥ አርባ ወታደሮች ለተገደሉበት በመኪና ላይ የተጠመደ ቦምብ ፍንዳታ ኃላፊነት የወሰደው ነው።

ህንድ በዛሬው የአየር ጥቃትዋ ብዛት ያላቸው ታጣቂዎች እንደተገደሉ አመልክታለች። ጥቃቱ በሁለቱ ኒውክሊየር ታጣቂ ተቀናቃኛ ሃገሮች መካከል ውጥረቱን ያባብሰዋል ተብሏል። ፓኪስታን በህንዱ ጥቃት የደረሰ ጉዳት የለም ብላለች።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG