ዋሺንግተን ዲሲ —
ህንድ ባለፈው የሃያ አራት ሰዓት ጊዜ ውስጥ ወደ አስራ አንድ ሺህ የሚጠጉ አዲስ የኮሮናቫይረስ ተጠቂዎች መመዝገቧን አስታውቃለች።
በዚህም ህንድ በተጠቂዎች ብዛት ቀዳሚውን ስፍራ ከያዘችው ከዩናይትድ ስቴትስ ከብራዚል እና ከሩሲያ ቀጥላ አራተኝነቱን ይዛለች።
የዩናይትድ ስቴትሱ ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ ባወጣው መረጃ መሰረት በአሁኑ ጊዜ በዓለም በጠቅላላ ካለው ከሰባት ነጥብ አምስት ሚሊዮን በላይ የኮሮናቫይረስ ተጋልጭ ውስጥ ህንድ ሁለት መቶ ዘጠና ሰባት ሺህ አምስት መቶ ሰላሳ አምስቱን ይዛለች።
ዩናይትድ ስቴትስ ቁጥሩ ከሁለት ሚሊዮን አልፉዋል፤ ብራዚል ከስምንት መቶ ሺህ ሩስያ ከአምስት መቶ አስር ሺህ በላይ ተጠቂዎች አሏቸው።