በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የህንድ የጠፈር አገልግሎት ሰው አልባ መንኮራኩር ወደ ጨረቃ ሊያመጥቅ ነው


የህንድ የጠፈር አገልግሎት በመጪው ሰኞ አንድ ሰው አልባ አሳሽ መንኮራኩር ወደ ጨረቃ ደቡባዊ ክፍል ለማምጠቅ ለሁለተኛ ጊዜ ሙከራ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

'Chandrayaan-2' የተባለው የጠፈር መንኮራኩር የሚመጥቀው የመጀመርያ ሙከራ ባደረገበት ሳምንት ነው። ባለፈው ሳምንት የተደረገው ሙከራ የከሸፈው መንኮራኩሩ ከመነሳቱ ከአንድ ሰዓት ባነሰ ጊዜ ውስጥ በተፈጠረ የቴክኒክ ችግር ነው ተብሏል።

'Chandrayaan-2' የሚመጥቀው ከጨረቃ ራቅ ብሎ በሚገኝ ቦታ ላይ አሉ የተባሉትን የውሀ ክምችቶችን ለማሰስና ለማጥናት የሚችል መሳርያ ለመላክ መሆኑ ተገልጿል። በፊት የተካሄደ የህንድ የጠፈር ተልዕእኮ የውሀ ክምችት መኖሩን አረጋግጧል ተብሏል።

የህንድ የ $140 ሚልዮን ዶላር ተልዕኮ ስኬት ካገኘ መንኮራኩሩን በጨረቃ ጠረፍ ላይ ተመቻችቶ ለማስረፍ በማስቻል ረገድ ህንድ አራተኛው ሀገር ትሆናለች ማለት ነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG