በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በህንድ ሰላማዊ ሰልፎች ተካሄዱ


ህንድ ከአጎራባች ሃገሮች የሚገቡ ሙስሊሞች ዜግነት እንዳይሰጣቸው የሚከለክለውን አዲሱን ህጓን በመቃወም በሃገሪቱ ዙሪያ ሰልፎች ተካሂደዋል።

ኒው ዴልሂ ውስጥ በሺዎች የተቆጠሩ የተቃውሞ ሰልፈኞች ከፖሊሶች ጋር ተጋጭተዋል። ፖሊስ አስለቃሽ ጋዝ ረጭቶባቸዋል፣ ሁለቱም ወገኖች ድንጋይ ተወራወረዋል።

አዲሱ ህግ ብዙሃን ህዝባቸው ሙስሊም ከሆኑ ከባንግላዴሽ፣ ከፓኪስታን እና ከአፍጋኒስታን ያለህጋዊ ፈቃድ የሚገቡ ሂንዱዎች ክርስቲያኖች እና ሌሎችም የህዳጣን የሃይማኖቶች ተከታዮች በተፋተነ መንገድ ዚግነት እንዲሰጣቸው ይፈቅዳል። አዲስ ህግ ሙስሊሞችን የማይመለከት መሆኑ በሀገሪቱ ዙሪያ ተቃውሞ ቀስቅሷል።

የዜግነት ጉዳይ ህጉን ሁለቱም ምክር ቢቶች ባለፈው ሳምንት በከፍተኛ ድምፅ አጽድቀዋታል።

ከህንድ ህዝብ ውስጥ ሰማኒያ ከመቶው የሂንዱ ዕምነት ተከታዮች ሲሆኑ አስራ አራት ከመቶው ማለትም ሁለት መቶ ሚሊዮን ህዝቡዋ የእስልምና ዕምነት ተከታዮች ናቸው። በዚህም ህንድ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የዕምነቱ ተከታዮች ካላቸው ሃገሮች መካከል አንዷ ነች።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG