በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሕንድ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ16 ሰዎች ሕይወት ጠፋ፤ ፍለጋው ቀጥሏል


በሕንድ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ16 ሰዎች ሕይወት ጠፋ፤ ፍለጋው ቀጥሏል
በሕንድ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ16 ሰዎች ሕይወት ጠፋ፤ ፍለጋው ቀጥሏል

በሕንድ፣ በሳምንቱ ውስጥ ከባድ ዝናም መጣሉን ተከትሎ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ፣ 16 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ፣ የአደጋ ሠራተኞች፣ አሁንም ከነሕይወታቸው በናዳ የተቀበሩ ሰዎችንና አስከሬኖችን ለማውጣት በፍለጋ ላይ ናቸው።

ናዳው፣ ራይጋድ በተሰኘው አውራጃ ከደረሰ በኋላ፣ 75 ሰዎችን በሕይወት ማውጣት እንደተቻለ፣ ባለሥልጣናት ተናግረዋል። ሌሎች በሕይወት ያሉ ሰዎች እና አስከሬኖች፣ አሁንም በፍርስራሹ ውስጥ ሳይኖሩ አይቀሩም፤ በሚል ፍለጋው ቀጥሏል።

በትላንትናው ዕለት በጣለው ከባድ ዝናም ምክንያት፣ ሌላ አደጋ እንዳይከሠት በመስጋት፣ ፍለጋው ተቋርጦ ነበር። በአደጋው አካባቢ ከሚገኙ 50 ቤቶች ውስጥ 17 የሚኾኑት፣ በመሬት መንሸራተቱ ተቀብረዋል፤ ሲሉ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

በሕንድ፣ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ብቻ፣ ከ100 በላይ ሰዎች፣ ከባድ ዝናም በአስከተለው አደጋ ሕይወታቸው አልፏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG