በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሞዲ ለታዳጊ ሀገሮች የኅብረት ጥሪ አሰሙ


 ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ
ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ

በማደግ ላይ ያሉ ሀገሮች መሪዎች በእሥራኤል እና በሃማስ ጦርነት የገጠሟቸውን ፈተናዎች ተጋፍጠው አንድነት እንዲኖራቸው የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ አሳሰቡ።

ሞዲ ይህን ማሳሰቢያ የተናገሩት ዛሬ (ዓርብ) በጠሩትና ከ100 በላይ ሀገሮች በተገኙበት የኢንተርኔት ላይ ጉባኤ ነው።

የዓለም ደቡብ ሀገሮች ለታላቅ ቁምነገር በአንድ ቃል የሚናገሩበት ጊዜ ደርሷል"

"የዓለም ደቡብ ሀገሮች ለታላቅ ቁምነገር በአንድ ቃል የሚናገሩበት ጊዜ ደርሷል" ብለዋል ሞዲ።

“የዓለም ደቡብ ድምፅ” የተባለው ጉባኤ የተዘጋጀው ኒው ደልሂ “ዲፕሎማሲያዊ ስኬት” ስትል የጠራችው ሲሆን ባለፈው መስከረም የተካሄደው የባለጠጎቹ ‘ቡድን ሃያ’ ሃገሮች ስብሰባም የአፍሪካ ኅብረት አባል እንዲሆን መወሰኑ ይታወሳል።

ህንድ እራሷን ደቡቡ መሪ አድርጋ የምትቆጥር ሲሆን ዓለም በቁልፍ ጉዳዮች ላይ ለሃገሮቹ የሚያደርገውን ድጋፍ ማሳደግ አለበት ባይ ናት።

የዓለም ደቡብ ሃገሮች ድምፅ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በጣም ልዩ ከሆኑ መሣሪያዎች አንዱ እንደሆነ የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ አክለው “ደቡብ ንፍቀ ክበብ በመልክአ ምድር ዕይታ ወትሮም የነበረ ቢሆንም የራሱ ድምፅ ሲኖረው ግን አሁን የመጀመሪያ ጊዜ ነው" ብለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG