በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ህንድ በቀይ ባሕር የባሕር ላይ ዘራፊዎችን የሚከታተሉ የጦር መርከቦች አሰለፈች


ፎቶ ፋይል፦ የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሱባራህማኛም ጃይሻንካራ
ፎቶ ፋይል፦ የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሱባራህማኛም ጃይሻንካራ

ህንድ ከቀይ ባሕር በስተምስራቅ መርከቦችን ከባሕር ላይ ዘራፊዎች የሚጠብቁ ቢያንስ አስራ ሁለት የጦር መርከቦች አሰልፋለች፡፡ ምዕራባውያን ኅያላን በኢራን የሚደገፉት የየመን ሁቲዎች በሚያደርሱት ጥቃት ላይ እያተኮሩ ባሉበት ባሁኑ ካሁን ቀደም ከተሰማራው ሁሉ የገዘፈ የባሕር ኅይል ያሰለፈችው ህንድ ያሰማራቸው ኅይሎች ከ250 የሚበልጡ መርከቦችን እየመረመሩ መሆናቸው ተዘግቧል፡፡

በዩናይትድ ስቴትስ የሚመራው የቀይ ባሕር ግብረ ኃይል ያልሆነችው ህንድ በዚያ ግብረ ኅይል ውስጥ የተሰማራ የጦር መርከብ አላሰማራችም፡፡ አደን ባሕረ ሰላጤ ግንባር ላይ ግን ሁለት የጦር መርከቦች ያቆመች ሲሆን ሰሜናዊ እና ምዕራባዊ የአረቢያ ባሕር ላይ ቢያንስ አእስር የጦር መርከቦች ከቅኝት አውሮፕላኖች ጋር ማሰማራቷን የህንድ ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡

ህንድ በአቅምም በጥቅምም እያደገች ስለሆነ እና ጥሩ ያላት እንደመሆኗ ችግሮች ሲፈጠሩ መርዳት አለባት”

የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሱባራህማኛም ጃይሻንካራ ባለፈው ማክሰኞ በሰጡት መግለጫ “ህንድ በአቅምም በጥቅምም እያደገች ስለሆነ እና ጥሩ ያላት እንደመሆኗ ችግሮች ሲፈጠሩ መርዳት አለባት” ብለዋል፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ፡ ቻይና እና ፈረንሳይን ጨምሮ ሌሎች ሀገሮች በቀይ ባሕር አካባቢ የባሕር ኅይል ያሰማሩ ሲሆን ህንድ ከሁሉም ግዙፉ የርሷ መሆኑን ትናገራለች፡፡

የየመን ሁቲዎች ካለፈው ህዳር ወዲህ በቀይ ባሕር ላይ በሚጓዙ መርከቦች ላይ ጥቃት እያደረሱ ሲሆን ጥቃቱን የሚፈጽሙት ከእስራኤል ጋር የሚዋጉ ፍልስጥዔማውያንን ለመደገፍ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG