በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መቆሚያ ያልተበጀለት የህንዱ ሁለተኛ ዙር የኮቪድ 19 ማዕበል


ኮቪድ 19 በህንድ
ኮቪድ 19 በህንድ

ህንድን እያናወጠው ያለው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዛሬ 13ተኛ ቀን በተከታታይ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው ለቫይረሱ መጋለጡ ተዘግቧል። በአንድ ቀን ዕድሜ 357 ሺህ 229 አዲስ ለኮረናቫይረስ የተጋለጡ ሰዎች መዘገባቸውን የጤና ሚንስትር በዛሬው ዕለት አስታውቋል። ባለፉት ሃያ አራት ሰዓታት ውስጥ በደቡባዊ እስያዊቱ አገር በኮቪድ-19 ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉት ከ3449 በላይ ሰዎች ናቸው።

በጃን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ የኮረናቫይረስ መረጃ ማዕከል አሃዞች መሰረት ባሁኑ ወቅት በህንድ ለቫይረሱ የተጋለጠው ሰው ቁጥር ሃያ ሁለት ሚልዮን ነጥብ ሁለት በዚያች አገር በኮቪድ ሳቢያ ህይወቱ ያለፈው ሰው ቁጥር 222,408 ደርሷል። ያም ህንድን በወረርሽኙ ጥናት እና ለቫይረሱ በተጋለጡ ሰዎች ቁጥር ከዩናይትድ ስቴትስ ቀጥሎ ሁለተኛዋ አገር ያደርጋታል። በሟቶች ቁጥር ደግሞ ሶስተኛዋ አገር ናት።

በአንድ የኒው ዲልሂ ሆስፒታል ሃኪሞች የኮረናቫይረስ ወረርሽኝ ያስከተለው ቀውስ የሕክምና መስጫ ተቋሙ ከሚችለው በላይ ለማስተናገድ የተገደደበት ሁኔታ መፈጠሩን ይናገራሉ።

ዶ/ር ሩሺ ጉብታ በአንድ ማዕከላዊ ኒው ዴልሂ በሚገኝ ሆስፒታል የጽኑ ህሙማን መርጃ ክፍል ሃኪም ናቸው።

“አጋዥ ከማጣት የመጣ አይደለም። ጨርሶ ከመውደቅ ደረጃ መድረሱ እንጂ! ለሌላ ለማዘን ከምንችልበት ቦታ አይደለንም። እዚህ ታካሚዎች እየሞቱብን ነው። ይሄ የተለየ ድብቅ ምክኒያት የከሰተውም አይደለም።በተጨባጭ የሚታይ ነገር ነው። ሁሉም ያውቀዋል፡፡ አገረ ገዥው ያውቁታል። አስተዳደሩም ያውቀዋል። ሁሉም ያውቀዋል፡፡” ብለዋል።

ዶ/ር ጉብታ አክለውም መሠረታዊ የኦክስጂን አቅርቦት ያለመኖሩን እና ያላቸውም በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ሊያልቅባቸው እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

ትናንት የሆስፒታላቸው የድንገተኛ ክፍል ሞልቶ ስለነበር ከኮቪድ 19 ውጭ ሌሎች የድንገተኛ እርዳታ የሚሹ ታካሚዎችን ተቀብለው መርዳት ሳይቻላቸው መቅረቱን አስረድተዋል።

በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ሆስፒታሎች የህሙማን መቀበያ እና መርጃ መኝታዎች በመሙላታቸው እና ከፍተኛ የኦክስጂን አቅርቦቶች ዕጥረት በመፈጠሩ ለህልፈት የሚዳረጉ ሰዎች እንዲጨምር ማድረጉ ተገልጿል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ህንድ በገጠማት ችግር ሳቢያ ለደሃና መካከለኛ ገቢ ላላቸው አገሮች የሚሰራጨውን ክትባት የሚያመርተው የመድሃኒት ኩባንያ ብዙ ተስፋ እንደተጣለበት ማቅረብ በሚችልበት ሁኔታ ውስጥ ባለመሆኑ የዩናይድ ስቴትሱ የመድኃኒት አምራች ኩባንያ ሞደርና በዓለም ጤና ድርጅት አማካኝነት ለተቋቋመው ዓለም አቀፍ የክትባት ፕሮግራም COVAX የCOVID-19 ክትባቱን መጠኑ 500 ሚሊዮን የሚደርስ ክትባት ለማቅረብ ቃል መግባቱን በትላንትናው ዕለት ይፋ አድርጓል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

መቆሚያ ያልተበጀለት የህንዱ ሁለተኛ ዙር የኮቪድ 19 ማዕበል
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:04 0:00


XS
SM
MD
LG