በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19 በዓለም


ህንድ ውስጥ በትናንትናው ዕለት 81,466 አዲስ የኮሮናቫይረስ ተጋላጮች መመዝገባቸውን የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ይህ በሀገሪቱ ባለፉት ስድስት ወራት በአንድ ቀን ከተመዘገቡት አሃዞች ሁሉ ከፍተኛው መሆኑንም ገልጿል። ከዩናይትድ ስቴትስ እና ከብራዚል ቀጥሎ ከፍተኛው ቁጥር ያላት ህንድ በአሁኑ ጊዜ የቫይረሱ ተጋላጮች ቁጥር ከ12 ነጥብ ሦስት ሚሊዮን ማለፉ ታውቋል።

ዩናይትድ ስቴትስ 30 ነጥብ 5 ሚሊዮን፣ ብራዚል ደግሞ 12 ነጥብ 8 ሚሊዮን መድረሱን የጆንስ ሃፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የኮቪድ-19 መረጃ ማዕከል ይጠቁማል። በዓለም ዙሪያ ያለው የቫይረሱ ተያዦች ቁጥር ደግሞ ከ129 ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ማለፉን የማዕከሉ መረጃ ያሳያል።

XS
SM
MD
LG