የቡድን 20 ጉባዔ መጠናቀቅን ተከትሎ፣ ህንድ እና ሳዑዲ ዓረብያ የኢኮኖሚ እና የደህንነት ትብብራቸውን ለማስፋፋት ተስማምተዋል።
የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ እና የሳዑዲ ዓረብያው ልዑል አልጋ ወራሽ መሃመድ ቢን ሳልማን ሰኞ ዕለት ኒው ደሊ ላይ ተገናኝተዋል፡፡
ሁለቱ መሪዎች በኢኮኖሚ፣ መከላከያ፣ ፖለቲካ እንዲሁም በሌሎች መስኮች የሁለቱን ሀገራት ትብብር ለማሳደግ ተስማምተዋል።
ባላፈው ቅዳሜ የቡድን 20 መሪዎች ህንድን ከመካከለኛው ምሥራቅ እና አውሮፓ የሚያገናኝ የባቡር እና የመርከብ ኮሪደር ለመገንባት ማቀደቻን አስታውቀዋል።
በቡድን 20 ጉባዔ ላይ እንደተገለፀው፣ ኮሪደሩ የንግድ ልውውጥን ለማሳደግ ፣የኃይል አቅርቦትን ለማዳረስ እና የዲጂታል ግንኙነትን ለማሻሻል ይረዳል ተብሏል።
ፕሮጀክቱ ሕንድ፣ ሳዑዲ ዓረቢያ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ፣ ዮርዳኖስ፣ እስራኤል እና የአውሮፓ ኅብረትን እንደሚጨምር በአሶሴይትድ ፕሬስ ዘገባ ላይ ተመልክቷል።
በህንድ እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህንዳውያን ስደተኞች በሠራተኝነት በሚያገለግሉባት ሳዑዲ ዓረቢያ መካከል ያለው የንግድ ግንኙነት ባለፉት ዓመታት ዕድገት አሳይቷል ተብሏል።
መድረክ / ፎረም