በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ህንድና ጃፓን ለትብብራቸው የጋራ የጦር ልምምድ አቅደዋል


የህንድ መከላከያ ሚኒስትር ራንጅት ሲንግ ከጃፓኑ አቻቸው ያሱኮዙ ሃማዳ ጋር ቶኪዮ ውስጥ
የህንድ መከላከያ ሚኒስትር ራንጅት ሲንግ ከጃፓኑ አቻቸው ያሱኮዙ ሃማዳ ጋር ቶኪዮ ውስጥ

ህንድና ጃፓን ወታደራዊ ህብረታቸውን በማጠንከር ተጨማሪ የጋራ የጦር ልምምዶችን እንደሚያደርጉ አስታወቁ፡፡

ኒውደልሂ የመከላከያ ኃይሏን ለማጠንከር የጃፓን ኢንደስትሪዎች ኢንቨስት እንዲያደርጉ መጋበዟንም ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

የህንድ መከላከያ ሚኒስትር ራንጅት ሲንግ ከጃፓኑ አቻቸው ያሱኮዙ ሃማዳ ጋር ቶኪዮ ውስጥ የተነጋገሩ ሲሆን ከውጭ ጉዳዮ ሚኒስትሮቻቸው ጋር በሚደረገው የጋራ ውይይም ላይ ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡

ህንድ ልክ ጃፓን እንደምታደርገው ሁሉ፣ ጎረቤቷ ቻይናን ጨምሮ ያለውን ወታደራዊ ስጋት ለመከላከል የራሷን ጦር ማጠናከር መያዟ በዘገባው ተመልክቷል፡፡

ሁለቱ አገሮች ከአውስትራሊያና ዩናይትድ ስቴትስ ጋር፣ “አራቱ ቡድኖች” (the Quad group) ተብሎ የሚታወቀው የ4 አገሮች ስብሰብ አባል ናቸው፡፡

XS
SM
MD
LG