ሕንድ ለአፍሪካ ሃገሮች ብድር አስር ቢሊዮን ዶላር መደበች
ከአርባ የሚበልጡ የአፍሪካ ርዕሳነ ብሔራት የተካፈሉበት የሕንድና ኣፍሪካ የመሪዎች ጉባዔ ኒውዴልሂ ውስጥ ተካሂዱዋል። ሕንድ በጉባዔው ላይ ከአፍሪካ ሃገሮች ጋር ጥብቅ ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ትስስር ለመመስረት ብርቱ ጥረት ማድረጉዋን አንጃና ፓስሪቻ(Anjana Pasricha) ከስፍራው ለቪኦኤ ያጠናቀረው ዘገባ ኣመልክቱዋል። ሕንድ የአፍሪካን ልማት ለማገዝ የሚውል የአስር ቢሊዮን ዶላር አዲስ ብድር መመደብዋ በጉባዔው ላይ ይፋ ተደርጉዋል። ሙሉውን ዝርዝር ይህንን ፋይል በመጫን ለማምበብ ይችላሉ። ይህ አሶሽየትድ ፕረስ የላከው የፎቶ መድብል ነው።