በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሕንድ ለአፍሪካ ሃገሮች ብድር አስር ቢሊዮን ዶላር መደበች


የሕንድና ኣፍሪካ የመሪዎች ጉባዔ
የሕንድና ኣፍሪካ የመሪዎች ጉባዔ

ከአርባ የሚበልጡ የአፍሪካ ርዕሳነ ብሔራት የተካፈሉበት የሕንድና ኣፍሪካ የመሪዎች ጉባዔ ኒውዴልሂ ውስጥ ተካሂዱዋል። ሕንድ በጉባዔው ላይ ከአፍሪካ ሃገሮች ጋር ጥብቅ ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ትስስር ለመመስረት ብርቱ ጥረት ማድረጉዋን አንጃና ፓስሪቻ(Anjana Pasricha) ከስፍራው ለቪኦኤ ያጠናቀረው ዘገባ ኣመልክቱዋል። ሕንድ የአፍሪካን ልማት ለማገዝ የሚውል የአስር ቢሊዮን ዶላር አዲስ ብድር መመደብዋ በጉባዔው ላይ ይፋ ተደርጉዋል።

በዓለም ምጣኔ ሃብት ሁለቱ ብሩህ የተስፋ እና የመልካም ዕድል ስፍራዎች ህንድና አፍሪካ ሲሉ የጠሩዋቸው የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በአጋርነት ተሳስረን ለብልጽግና እንሰራለን ” በማለት ቃል ገብተዋል።

“ካይሮን ከኬፕታውን፡ ማራኬሽን ከሞምባሳ በማገናኘት አፍሪካን እንረዳለን። የመሠረተ ልማት፡ የሓይል ምንጭና የመስኖ እንዲያድግ እናግዛለን። የአፍሪካ የተፈጥሮ ሃብት ዋጋ እንዲያድግ፡ የኢንዱስትሪና የመረጃ ቴክኖሎጂ ፓርኮች እንዲቁዋቁዋሙ እንረዳለን።”

የሕንድና ኣፍሪካ የመሪዎች ጉባዔ

ይህ ሶሥተኛው የህንድና የአፍሪካ የመሪዎች ጉባዔ፡ ህንድ ከምንጊዜው ይበልጥ በአህጉሪቱ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ጥረት ያደረገችበት ከመሆኑም በቀር ሃምሳ ኣራቱም አገሮች በሙሉ ተወክለውበታል።

በጉባዔው ላይ ከተሳተፉት የአፍሪካ ርዕሳነ ብሄራት መካከል፡ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚደንት ጄኮብ ዙማ፡ የዚምባቡዌው ሮበርት ሙጋቤ፡ የናይጄሪያው ሙሃማዱ ቡሃሪ እና የግብጹ አብደልፋታህ ኤል ሲሲ ይገኙባቸዋል። በትናንት ረቡዕ ማታው ኦፊሴላዊ የራት ግብዣ ላይ ብዙዎቹ መሪዎች በቀለማት በደመቀ የህንድ የአገር ባህል ልብሶች ታይተዋል።

ህንድ በአህጉረ አፍሪካ እጅግ የጠነከረ መሰረት እየጣለች እንዳለችው እንደቻይና ሁሉ የጠበቀ የምጣኔ ሃብት ትስስር ለመመስረት ትሻለች። ይህን ማድረጉዋ በአፍሪካ ግዙፍ የተፈጥሮ ሃብት በተለይም ደግሞ በነዳጅ ዘይት ሃብቱዋ ልትጠቀም ስለምትፈልግ ነው። በርግጥም ህንድ ከአፍሪካ ጋር ያላት የንግድ ትስስር

በእጥፍ ጨምሮ ባለፉት አስር ዓመታት ውስጥ ሰባ ቢሊዮን ዶላር ደርሱዋል። ከኣፍሪካ ሀገሮች ጋር በዓመት በሁለት መቶ ቢሊዮን ዶላር ከምትናገደው ከቻይና ጋር ግን ኣትወዳደርም።

የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ ስለሀገራቸውና ስለኣአፍሪካ የተጠናከረ የንግድና መዋዕለ ነዋይ ትስስር አውስተዋል። ሀገራቸው ለአፍሪካ ሃገሮች በአዲስ ብድር መልክ የሚሰጥ አስር ቢሊዮን ዶላር መመደቡዋን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለልማት ርዳታ ደግሞ ሌላ ስድስት መቶ ሚሊዮን ዶላር መመደቡዋን ይፋ አድርገዋል።

የሕንድና ኣፍሪካ የመሪዎች ጉባዔ

ኣብዛኛው ርዳታ የሚውለው ጤና ጥበቃ፡ ውድ ያልሆኑ መድሃኒቶች ተደራሽነት፡ ግብርና እና ቴክኖሎጂን በመሳሰሉ ዘርፎች ላይ ለሚያተኩሩ ቴክኒካዊና ትምህርታዊ ተቁዋማት መሆኑ ተመልክቱዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ በተጨማሪም በመጪው ህዳር ወር ፈረንሳይ ፓሪስ ላይ በሚከፈተው የዓለም መሪዎች የአየር ንብረት ጉባዔ ላይ ለማስተዋወቅ በሚፈልጉትና “የጸሐይ ሃይል ባለጸጋ ሃገሮች” ባሉት ህብረት የአፍሪካ ሃገሮች እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።

“በህንድና በኣፍሪካ ጸሐይ ስትጠልቅ በብዙ አስር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ መኖሪያ ቤቶች በጨለማ ይዋጣሉ። ህዝቦቻችንን ብርሃን እንዲፈነጥቅላቸው የኤሌክትሪክ ሃይል እንዲዳረስላቸውም እንፈልጋለን። ያን ማድረግ የምንፈልገው ግን የኪሊማንጃሮን በረዶ አቅልጦ በማያጠፋ፡ የጋንጋን ወንዝ የሚመግበውን የበረዶ ግርር በማይደመስስና ደሴቶቻችንን በማያወድም መንገድ ነው።”

ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ በማስከተል አገራቸውና አፍሪካ በዓለም አቀፍ የንግድ ድርድሮች ውስጥ የታዳጊ ሃገሮች ስጋቶች መንጸባረቃቸውን ለማረጋገጥ “በአንድ ድምጽ” እንዲናገሩና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን በመሳሰሉ ተቁዋማት ለውጥ እንዲካሄድ ግፊት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ሙሉውን ዝርዝር ያዳምጡ።

ሕንድ ለአፍሪካ ሃገሮች ብድር አስር ቢሊዮን ዶላር መደበች
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:29 0:00

XS
SM
MD
LG