ዋሺንግተን ዲሲ —
ህንድ በዛሬው ዕለት ከምንጊዜው ከፍተኛ የሆነውን የኮሮናቫይረስ ተያዦች ቁጥር እንደመዘገበች አስታወቀች።
ባለፈው የሃያ አራት ሰአት ጊዜ ብቻ 131,968 ቫይረሱ የያዛቸው ሰዎች እንደተገኙ የጤና ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
በአውሮፓ በኮቪድ-19 ምክንያት ጽኑ ህሙማን ህክምና ክፍል ያሉት ሰዎች ቁጥር ወደ 4,500 መጠጋቱን የገለጹት የጀርመን የጤና ሚኒስትር፣ በዚህ ከቀጠለ ከሀገራችን የጤና ጥበቃ መዋቅር ዐቅም በላይ ይሆንል ብለን እንሰጋለን፣ እንቅስቃሴዎችን መዝጋት አለብን ብለዋል።