በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19 በህንድ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ህንድ በኮቪድ-19 ምክንያት የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከሃምሳ ሽህ ማለፉን አስታወቀች። ዛሬ ብቻ ከዘጠኝ መቶ የሚበልጡ ህሙማን እንደሞቱ ገልፃለች።

ህንድ በኮቪድ-19 ምክንያት በሞቱ ሰዎች ብዛት ዩናይትድ ስቴትስ ብራዚልና ሜክሲኮን በአራተኝነት እየተከተለች ነው።

በሌላ በኩል ኒውዚላንድ ከአንድ መቶ ለሚበልጡ ቀናት በማኅበረሰቦች ውስጥ አንድም የሚታወቅ አዲስ የኮሮናቫይረስ ያለመገኘቱን ስኬቷን እያከበረች መቆየቷን ተከትሎ አዲስ ተግላጮች በመገኘታቸው የምርጫ የጊዜ ሰሌዳዋን አራዝማለች።

በዚህም መስረት በሚቀጥለው ወር ሊካሄድ የነበረው ምርጫ እኤአ ወደ ጥቅምት አስራ ሰባት ቀን ተዛውሯል፤ ከዚያ ግን አያልፍም ብለዋል የኒውዚላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አህደርን።

ደቡብ ኮሪያም የኮሮናቫይረስ ሥርጭትን በመቆጣጠር ከፍተኛ ስኬት ማስዝገቧ ሲታወቅ በአሁኑ ወቅት በዋና ከተማዋ ሶል አዲስ የቫይረሱ ተጋላጮች ከተገኙ በኋላ የጤና ባለሥልጣናት ስርጭቱን ለመቆጣጠር ጥረት እያደረጉ ናቸው።

በሌላ ዜና ጃፓን በኮቪድ-19 ምክንያት ዓመታዊ የኢኮኖሚ ይዞታዋ ካለፈው ሚያዝያ እስከ ሰኔ በነበረው ወቅት በሃያ ሰባት ነጥብ ስምንት ከመቶ ማሽቆልቆሉን ተናግራለች።

XS
SM
MD
LG