በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢንተርኔት ጉዳይ የሩሲያና የአሜሪካ ፍጥጫ


ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ
ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ

የኦባማ አስተዳደር ወደ ፍፃሜው እየተቃረበ በመጣ መጠን የዋሺንግተንና የመስኮብ ግንኙነት ከድጡ ወደ ማጡ እየተንሸራተተ ይበልጥ እየሻከረ ሲሄድ እያየን ነው፡፡

ሩሲያ ባለፈው ጥቅምት 29 የተደረገውን የአሜሪካ አጠቃላይ ምርጫ ውጤት ለማዛባት አስባ እንደነበር፤ እንዲያውም በኢንተርኔት ጣልቃ ገብታ ብዙ ሙከራ ማድረጓን አንስተው ለዓለም የተናገሩት ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ አስፈላጊ በሆነ ጊዜና ቦታ የአፀፋ እርምጃ እንወስዳለን ያሉ ጊዜ እንደምን ይሆን ተሰናባች ፕሬዚዳንት "አንካሳው ዳክዪ እንዲህ ዓይነት ዛቻ የሚያሰሙት? መቼና እንዴትስ ሊያደርጉት ነው?ያሉ ነበሩ፡፡

በተለይ በብዙው ጉዳይ የፕሬዚዳንት ኦባማን ሥራ ሁሉ 'አፈርሳለሁ' አያሉ የሚዝቱ ተተኪ ተመራጭ ፕሬዚዳንት አልጋውን ለመረከብ ቀናት እየቆጠሩ ባሉበት ሁኔታ፡፡ ተመራጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሩሲያ እንዲህ ዓይነቱን የድብቅ የኢንቴርኔት ወረራና ጥቃት ተግባር ፈፅማለች ብለው እንደማያምኑ በተደጋጋሚ ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጂ የአሁኑ ፕሬዚዳንት ኦባማ ትናንት የመጀመሪያውን እርምጃቸውን ወሰዱ፤ በዚያ ሩሲያን በሚከሰሱበት የኢንተርኔት ድብቅ ወረራና ጥቃት ውስጥ ከሩሲያ ከፍተኛ መሪዎች ቀጥተኛ መመሪያ እየተቀበሉ ያስፈፅሙ ነበር ያሏቸውን 34 የሩሲያ ዲፕሎማቶችና የምሥጢር ተልዕኮ አከናዋኞች በሰባ ሁለት ሰዓታት ውስጥ አሜሪካን ለቅቀው እንዲወጡ አዝዘዋል /‘ፔርሶና ኖን ግራታ’ ይባላል - በዶፕሎማሲው ቋንቋ/ ሲሉ ጠሯችውና ግንኙነታቸውን ቆረጡ፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያድምጡ፡፡

በኢንተርኔት ጉዳይ የሩሲያና የአሜሪካ ፍጥጫ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:32 0:00

XS
SM
MD
LG