በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዉሃን ያቀኑት የዓለማቀፍ የጤና ድርጅት ባለሞያዎች ከለይቶ ማቆያ ወጡ

ኮቪድ-19 መጀመሪያ የታየባት ዉሃን ከተማ ምርምር ለማድረግ የሄዱ የዓለም አቀፍ የጤና ድርጅት ባለሞያዎች፣ ለሁለት ሳምንታት ተቀምጠውበት ከነበረ ለይቶ ማቆያ ሆቴላቸው ሲወጡ
ኮቪድ-19 መጀመሪያ የታየባት ዉሃን ከተማ ምርምር ለማድረግ የሄዱ የዓለም አቀፍ የጤና ድርጅት ባለሞያዎች፣ ለሁለት ሳምንታት ተቀምጠውበት ከነበረ ለይቶ ማቆያ ሆቴላቸው ሲወጡ

ኮቪድ-19 መጀመሪያ የታየባት ዉሃን ከተማ ምርምር ለማድረግ የሄዱ የዓለም አቀፍ የጤና ድርጅት ባለሞያዎች፣ ለሁለት ሳምንታት ተቀምጠውበት ከነበረ ለይቶ ማቆያ ሆቴላቸው ዛሬ ወጡ።

እነዚህ ዓለም አቀፍ ቡድኖች ዛሬ ከሰዓት በኋላ ከነበሩበት ሆቴል ሲወጡ ታይተዋል። የኮሮና ቫይረስ መነሻን ምክኒያቱን ለማወቅ ምርምር እንዲደረግ ይቀርብ የነበረውን ጥያቄ ቻይና ለረዥም ወራት ስትከላከል ቆይታ የነበረ ሲሆን በመጨረሻም ፈቃድ ሰጥታለች።

ቡድኑ ከዚህ በኋላ በሚኖረው ቆይታ ከምርምር ማዕከል ተቋማት፣ ከሆስፒታሎች፣ ከገበያ ቦታ እና ቫይረሱ ተነስቶበታል ከሚባለው አካባቢ የሚገኙ ሰዎችን በማነጋገር ብዙ ሳምንታትን ያሳልፋሉ ተብሎ ተገምቷል።

XS
SM
MD
LG