ዋሺንግተን ዲሲ —
በአናሳዋ የምዕራብ አፍሪካ ሀገር ቶጎ ውስጥ ትናንት ረቡዕ የተቀሰቀሰው ሕዝባዊ አመፅ፣ ከሃምሳ ዓመታት በላይ የዘለቀው የፕሬዚደንት ፋውራ ናሲንጌ ንጉሣዊ አገዛዝ እንዲያከትም መጠየቁ ተሰማ።
በቶጎ ተቃዋሚ ፓርቲዎች መሪዎች ቅስቀሳ የተካሄደውና በብዙ መቶ ሺህዎች የሚቆጠር ሕዝብ የተካፈለበት እንቅስቃሴ፣ ፕሬዚደንት ናሲንጌ ሥልጣናቸው እአአ በ2020 ሲጠናቀቅ ዳግም ወደ አመራር እንዳይመለሱና፣ የፕሬዚደንታዊ የሥልጣን ዘመን እንዲወሰንም የህገ መንግሥት ማሻሻያ እንዲደረግ ጠይቋል።
በመሠረቱ ቶጎ ውስጥ ፕሬዚደንታዊ የሥልጣን ዘመን በሁለት ዓመታት እንዲወሰን ቀደም ብሎ እአአ 1992 ተደንግጎ የነበረውን፣ የወቅቱ መሪ የናሲንጌ ወላጅ አባት ናሲንጌ እያደማ ከአሥር ዓመታት በፊት እንደሰረዙት ታውቋል።
ባለፈው ነሐሴ ወርም ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ተካሂዶ ሁለት ሰዎች እንደሞቱ አይዘነጋም።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ