በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፓኪስታን የታጠቁ አማጽያን ባደረሱት ጥቃት 34 ሰዎች ተገደሉ


ፓኪስታን ውስጥ የታጠቁ አማጽያን ባካሄድዋቸው የተለያዩ ጥቃቶች ቢያንስ 34 ሰዎች ተገድለው በርካታ ሌሎች ቆስለዋል።

ፓኪስታን ውስጥ የታጠቁ አማጽያን ባካሄድዋቸው የተለያዩ ጥቃቶች ቢያንስ 34 ሰዎች ተገድለው በርካታ ሌሎች ቆስለዋል።

ካራቺ በተባለችው ደቡባዊት ከተማ ያሉት ባለሥልጣኖች በገለፁት መሰረት የታጠቁ ሦስት አጥፍቶ ጠፊዎች የቻይና ቆንስላን ባጠቁበት ወቅት ቢያንስ 4 ሰዎች ተገድለዋል።

“ሬንጀርስ” የተባሉት እግረኛ ወታደሮች ቃል አቀባይ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ከአጥቂዎቹ አንዱ በቆንስላው የቪዛ ክፍል በር ላይ ራሱን አፈነዳ። ዓላማው ተባባሪዎቹ ወደ ቆንስላው እንዲገቡ ለማማቻቸት ነበር ብለዋል።

አጥቂዎቹ ወደ ቻይናው ቆስላ ገብተዋል የሚለውን ወሬ ቃል አቀባዩ አስተባብለዋል። ሁለቱ ሌሎች አጥፍቶ ጠፊዎች ቆንስላውን ይጠብቁ በነበሩ የፓኪስታን ወታደሮች ተገደለዋል ብለዋል።

ከጥቂት ሰዓታት በኋላ በሰሜን ምስራቅ ኦራከዛይ ክልል በፈነዳ ከብድ ቦምብ ቢያንስ 30 ሰዎች ተገድለዋል። ከ40 በላይ ደግሞ ቆስለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG