በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሳይበርና ዲጂታል ቢሮ ሊያቋቁም ነው


ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት
ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት

ዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሳይበርና የዲጅታል ፖሊሲ ቢሮ ሊያቋቁም ማቀዱን አስታወቀ፡፡ ሚኒስቴሩ ይህን ያስታወቀው በዩናይትድ ስቴትስ ኢንተርኔት፣ አውታረ መረብና መሠረት ልማቶች ላይ የእገታና የጠለፋ ጥቃቶች እየጨመሩ መምጣታቸውን መሠረት በማድረግ ነው፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ፣ በህግ መወሰኛው ምክር ቤት የጸደቀ፣ ቢሮውን የሚመራ “ልዩ አምባሰደር” እንደሚሠየምም አስታውቀዋል፡፡ በዚህ ዓመት፣ ጠላፊዎች በርካታ የዩናይትድ ስቴትስ ድርጅቶችን፣ አውታረ መረቦች መጥለፋቸው ተመልክቷል፡፡

ከእነዚህ ውስጥ፣ ግዙፉን የኮሎኒያል የጋዝ ማስተላለፊያ መስመርን በመጥለፍ፣ በምስራቅ ዩናይትድ ስቴትስ የሚገኘውን የአገልግሎት መስመር አውከዋል፡፡ መሰረቱን በአይዋ ክፍለ ግዛት ያደረገውን የግብርና ኩባንያ ጠልፎ በማገት፣ የመካከለኛውን ምዕራብ የሰብል እርሻ ሂደትን አስተጓጉለዋል፡፡ ጠላፊዎቹ ትላልቅ አውታረ መረቦችን ካገቱ በኋላ ከፍተኛ ገንዘብ ይጠይቃሉ፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከሁለት ሳምንት በፊት በሰጠው መግለጫ፣ ጠላፊዎች፣ በዚህ ዓመት የስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ብቻ፣ 590 ሚሊዮን ዶላር የተከፈላቸው መሆኑን አስታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG