በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ልጆች ከትምህርት ቤት ውጪ ሆነዋል - ዩኒሴፍ


የዩኒሴፍ ጄኔቫ፣ ስዊዘርላንድ
የዩኒሴፍ ጄኔቫ፣ ስዊዘርላንድ

በግጭት፣ ሁከት፣ የተፈጥሮ አደጋዎች እና መፈናቀል ሳቢያ በኢትዮጵያ ከ9 ሚሊዮን በላይ የሚኾኑ ልጆች ከትምህርት ቤት ውጪ እንደሆኑና፣ ከ9 ሺሕ በላይ የሚሆኑ ትምህርት ቤቶችም እንደተዘጉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል።

የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት በምኅጻሩ ዩኒሴፍ፣ በአወጣው ዓመታዊ ሪፖርት እንዳለው፣ ከትምህርት ውጪ እንዲሆኑ ከተደረጉት አዳጊዎች ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የሚገኙት በአማራ ክልል ሲሆን፣ 4.4 ሚሊዮን ይሆናሉ። በመቀጠልም በኦሮሚያ ክልል 3.2 ሚሊዮን፣ እንዲሁም በትግራይ ክልል ደግሞ 1.2 ሚሊዮን ይሆናሉ።

በኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፉ በግጭት፣ በተፈጥሮ አደጋዎች እና በመፈናቀል ምክንያት ችግር እንደገጠመው ዩኒሴፍ አመልክቷል።

በኢትዮጵያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ልጆች ከትምህርት ቤት ውጪ ሆነዋል - ዩኒሴፍ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:32 0:00

“በሃገሪቱ ከ10ሺሕ በላይ የሚሆኑ ወይም 18 በመቶውን የሚወክሉ ትምህርት ቤቶች በግጭትና በአየር ንብረት አደጋዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፣ ይህም ደህንነቱ የተጠበቀ እና በሥራ ላይ የሚገኝ የትምህርት አገልግሎት ተደራሽነት እንዲቀንስ አድርጓል” ሲል ድርጅቱ ባወጣው ሪፖርት አክሏል።

የሚኒስቴሩ የትምህርት ፕሮግራሞችና ጥራት ማሻሻያ መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ዮሐንስ ውጋሶ፣ የዩኒሴፍ የመረጃ አወሳሰድ ሂደት የተለየ መኾኑ ለቅጥሩ ከፍ ማለት ምክኒያት ሊኾን እደሚችል ለቪኦኤ ተናግረዋል።

ባለፈው መስከረም በአማራ ክልል፣ ምሥራቅ ጎጃም ሁለት መምህራን ተገድለዋል። ይህም በአካባቢው በትምህርት ዘርፍ በተሰማሩት ላይ ፍርሃት እንደፈጠረ ተነግሯል። የአካባቢው አስተዳደር ስም ሳይጠቅስ “በአማራ ሕዝብ ስም የሚምሉ” ያላቸው ቡድኖችን ለግድያው ተጠያቂ አድርጓል።

በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ አማጺ ቡድኖች፣ መምህራንን ኢላማ አለማድረጋቸውን አስታውቀዋል። ትምህርት ቤት መከፈቱን የሚቃወሙት “ለተማሪዎቹና ለማኅበረሰቡ ደህንነት ነው” ሲሉ አስታውቀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ እስካለፈው ኅዳር ወር መጨረሻ ድረስ በኦሮሚያ ክልል ከ9 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በወባ መያዛቸውንና 1ሺሕ 267 ደግሞ መሞታቸውን የዩኒሴፍ ሪፖርት አመልክቷል። ይህም በመላ ሃገሪቱ በበሽታው ሕይወታቸውን ካጡት ውስጥ 40.9 በመቶ ሲሆን፣ በአማራ 23.5 በመቶ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ 9.1 በመቶ እንዲሁም በደቡብ ምዕራብ ደግሞ 7.5 በመቶ መሆኑን አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG