ዋሺንግተን ዲሲ —
ሰሜን ኮሪያ ዛሬ ሐሙስ ያስተላለፈችው አስታራቂ ወይም አስማሚ ሃሳብ፣ የደቡብ ኮሪያው የክረምት ኦሎምፒክ ውድድር የተሳካ እንደሚሆን ጠቋሚ ነው ተባለ። ይህም፣ ሰሜን ኮሪያ ላይ የተጣለውን የኢኮኖሚ ማዕቀብ ያቀላል የሚል እምነት እንዳሳደረ ነው የተገለፀው።
የሁለቱ ሀገሮች የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብሰባ ከተካሄደ በኋላ የፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡን መንግሥት ይፋ ባደረገው መግለጫ፣ ሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ ያሉ ኮሪያውያን፣ ነፃ በሆነ የመልሶ አንድነት ሕብረት ላይ እንዲያተኩሩና ለዚህም በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባ ጥሪ አቅርቧል።
ይህ የፕዮንግያንግ የሰላም ጥሪ፣ ደቡብ ኮሪያ አዘውትራ በሰሜን ኮሪያ ላይ ታደርገው ለነበረው ጫና አዎንታዊ መልስ እንደሆነም ተገልጧል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ