በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ምርጫ ቦርድ በታሰሩ የኦነግ አመራር አባላት ጉዳይ ለፓርላማ አቤቱታ አቀረበ


ምርጫ ቦርድ በታሰሩ የኦነግ አመራር አባላት ጉዳይ ለፓርላማ አቤቱታ አቀረበ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:37 0:00

ምርጫ ቦርድ በታሰሩ የኦነግ አመራር አባላት ጉዳይ ለፓርላማ አቤቱታ አቀረበ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ከሦስት ዓመት በላይ በእስር ላይ የሚገኙት የኦነግ አመራሮች ጉዳይ እንዳሳሰበው ገልጾ፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቤቱታ አቅርቧል።

ቦርዱ አቤታውን ያቀረበው፣ ኮሚቴ አቋቁሞ እስረኞችን ለመጎብኘት ላደረገው ሙከራ፣ ከኦሮሚያ ክልል ፈቃድ ባለማግኘቱ እንደኾነ፣ የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

ኦነግ በበኩሉ፣ እስረኞቹ በስጋት ላይ መኾናቸውን ገልጿል።

የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ እውነቱ አለነ፣ የቀረቡትን ደብዳቤዎች እንደማያስታውሱ ገልጸው፣ ጉዳዩን ቋሚ ኮሚቴው የመፍታት ሕጋዊ ሥልጣን እንደሌለው ገልጸው፣ መታየት ያለበት በፍርድ ቤት እንደኾነ ተናግረዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG