በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሰራዊት ከፍተኛ አመራር ላይ ማዕቀብ ጣለች


ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት
ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት

ዩናይትድ ስቴትስ በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች መሪ አልጎኒ ሀምዳን ዳጋሎ ሙሳ ላይ በሰሜን ዳርፉር ዋና ከተማ በኤል ፋሸር የደረሰውን ጥቃት ጨምሮ፤ ቡድኑ በሱዳን በሚያካሂዳቸው እንቅስቃሴዎች እንዲሁም የጦር መሳሪያዎችን እና ሌሎች ወታደራዊ ቁሳቁሶችን ግዢ ባላቸው ተሳትፎ በዛሬው ዕለት ማዕቀብ ጥላለች፡፡

የዳጋሎ ድርጊቶች የፈጥኖ ደራሽ ጦር ቡድኑ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ በሲቪሎች ላይ የሚፈጽሟቸውን የጦር ወንጀሎች፣ በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች እና የዘር ማጽዳት እና ጦርነትን ማቀጣጠል ያካትታል ሲሉ በዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ቢሮ ቃል አቀባይ ማቲው ሚለር በመግለጫው አስታወቀዋል፡፡

ከዩናይትድ ስቴትስ እና ከሌሎች አጋር ሀገራት የሚሰጣቸውን ማስጠንቀቂያ ከመተግበር ይልቅ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ቡድን እና ተባባሪ ሚሊሻዎች፤ ወሲባዊ ጥቃትን እና ዐረብ ባልሆኑ ቡድኖች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶችን ጨምሮ አሰቃቂ ድርጊቶችን መፈጸማቸውን ቀጥለዋል ሲል መግለጫው አክሎ አስታውቋል፡፡

አያይዞም በሱዳን የጦር ሃይል እና ፈጥኖ ደራሽ ቡድኖች መካከል የሚካሄደው ጦርነት ለብዙ አስር ሺዎች ሞት እንዲሁም ለ11 ሚሊየን ዜጎች በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት መፈናቀል ምክንያት በመሆን ከፍተኛ ውድመት አስከትሏል ብሏል፡፡ የሱዳን ዜጎች የሲቪል መንግስት ተመስርቶ ሰላም እና ፍትህን ይሻሉ ሲልም አክሏል፡፡

ይህ የዛሬው እርምጃም ግጭትን ያቀጣጠሉትን በተጠያቂነት በመያዝ የሚደረግ ቀጣይነት ያለው የዩናይትድ ስቴትስ ጥረት መሆኑን ያመለከተው መግለጫው ግጭት ለማስቆም እና ሰላምን ለመደገፍ ዩናይትድ ስቴትስ ያሏትን አማራጮች ትጠቀማለች ሲል አስፍሯል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG