በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከፕሬዝዳንታዊ ሥልጣን እሰከማስነሳት የሚደርስ ሕገ መንግስታዊ ሂደት Impeachment ምንነትና አንድምታ!


ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ “ሥልጣናቸውን ለግል የፖለቲካ ጥቅም አውለዋል” በሚል በዪናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የዲሞክራቲክ ፓርቲ አባላት ያቀረቡትን ክስ ተከትሎ ከሥልጣን ሊያስነሳ በሚያስችል የሕግ ሂደት ባለፈው ግንቦት ወር ከሥልጣናቸው የተነሱት በዩክሬይን የቀድሞዋ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር Marie Yovanovitch ዛሬ ከማለዳው አንስቶ ይፋ የምስክርነት ቃላቸውን በመስጠት ላይ ናቸው።

አምባሳደር Yovanovitch የፕሬዝዳንቱ የግል ጠበቃ ሩዲ ጁሊያኒ እና አጋሮቻቸው ያካሄዱት የአምባሳደሯ የሥራ ባልደረቦች እና ዲሞክራቶች የስም ማጥፋት ዘመቻ .. ያሉትን ተከትሎ ነው፤ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ከሃምሌ 2016ዓም እስካለፈው ግንቦት 2019ዓም ያገለገሉበትን ኃላፊነት ለቀው ወደ ዋሽንገተን እንዲመለሱ የተደረጉት።

ባለፈው ረቡዕ በተጀመረው ይፋ የምስክሮች ቃል የሚሰማበት ሥነ ሥርዓትና በእንግሊዝኛው አጠራር Impeachment በተባለው በዚህ የሕግ ሂደት ምንነት ዙሪያ የተጀመረው ቃለ ምልልስ ነው።

ለሁለት ሳምንታት በሚካሄደው በዚህ ይፋ የምስክሮች ድምጽ የሚሰማበት ሂደት በዩክሬይን የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ዊልያም ቴይለር እና በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የአውሮፓ እና የዩሬዥያ ጉዳዮች ረዳት ሚንስትር ጆርጅ ኬንት በተመሳሳይ ከትላንት በስቲያ የምስክርነት ቃላቸውን መስጠታቸው ይታወሳል። የምስክሮችን ቃል የመስማቱ ሂደት በመጭው ሳምንት ይቀጥላል። የሥርዓቱን ምንነትና አንድማታ፤ እንዲሁም ሂደቶቹን ተከታትለን በተከታታይ እንዘግባለን።

ሞያዊ ትንታኔውን የሚሰጡንን አቶ ደረጀ ደምሴ ቡልቶ በዩናይትድ ስቴትስ ሕገ-መንግስታዊ ጉዳዮችን በሚመለከቱ የክስ ሂደቶች ጭምር የተሳተፉ የሕግ ባለ ሞያ ናቸው።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ከፕሬዝዳንታዊ ሥልጣን እሰከማስነሳት የሚደርስ ሕገ መንግስታዊ ሂደት Impeachment ምንነትና አንድምታ!
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:25 0:00
ከፕሬዝዳንታዊ ሥልጣን እሰከማስነሳት የሚደርስ ሕገ መንግስታዊ ሂደት Impeachment ምንነትና አንድምታ!
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:24 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG