በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መጥፎ ዜና ያለ ማቋረጥ ሲሰማ …


ፕሮፌሰር ዮናስ እንዳለ ገዳ - የነርቭና የአዕምሮ ህክምና እና ምርምር እንዲሁም የሰው ልጅ ባሕሪያት ጥናት ልዩ ባለሞያ
ፕሮፌሰር ዮናስ እንዳለ ገዳ - የነርቭና የአዕምሮ ህክምና እና ምርምር እንዲሁም የሰው ልጅ ባሕሪያት ጥናት ልዩ ባለሞያ

አንዳንዱ ይሁነኝ ብሎ የሚፈጸም በሰዎች ላይ ጉዳት የሚያደርስ ጥቃት ነው። ሌላው ደግሞ የሃሰት ወሬ ነው ምንጩ። በተከታታይ በብዛት ሲሰማ ግን አንዳች አደጋ ማስከተሉ አይቀሬ ነው።

የተፈጥሮ አደጋዎንች እና በተለያዩ አካባቢዎች የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ጨምሮ ከሰው ልጅ ልቦና ጭንቀት የሚያሳድሩ እና ጥልቅ ሃዘን እንዲሰማን የሚያደርጉ ዜናዎች ዛሬ-ዛሬ በዓለም ዙሪያ በብዛት ይደመጣሉ።

ለመሆኑ በመደበኛ የመገናኛ ብዙኃንም ይሁን አንዳንዴ መሠረት የሌላቸው አሳዛኝ የሃሰት ወሬዎች ጭምር በሚሰሙባቸው የማሕበራዊ ትስስር ገጾች በደጋጋሚ እና ያለማቋረጥ መልካም ያልሆኑ ዜናዎችን መስማት በአንጎላችን ላይ የሳድረው ተጽዕኖ ይኖር ይሆን?

በእርግጥ የእነኚህ መንፈስ አዋኪ አሉታዊ ወሬዎች የየዕለት ገጠመኝ መሆን ከጊዜያዊ ስሜት ያለፈ የሚያስከትሉት የጤና መቃወስስ ይኖር ይሆን? ምንስ ማድረግ ይበጃል?

ባለፉት ጥቂት ወራት ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙዎችን ለህልፈት እና ለሥቃይ የዳረጉ ሁኔታዎች አስመልክቶ የሚሰሙ ዜናዎች እና ወሬዎች በተለይ በአንጎል እና በልብ ጤና ላይ፡ እንዲሁም በአጠቃላይ ጤናችን ላይ የሚያሳድሩትን ተጽዕኖ ለመመርመር የሥነ ልቦና ባለሞያ ጋብዘን አወያይተናል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

ክፍል አንድ - መጥፎ ዜና ያለ ማቋረጥ ሲሰማ …
please wait

No media source currently available

0:00 0:26:47 0:00


XS
SM
MD
LG