የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር፣ በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን ውስጥ ለሥራ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሁለት ተሸከርካሪዎቹ በታጣቂዎች እንደተወሰዱበትና በክልሉ የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ደግሞ፣ በአንድ ተሽከርካሪው ላይ ጥቃት እንደተፈጸመ አስታወቀ።
በኃይል የተወሰዱት ሁለቱ ተሽከርካሪዎች፣ ከፊንላንድ ቀይ መስቀል በርዳታ የተገኘ የሕክምና ቁሳቁስ የያዙ እንደነበሩ፣ የማኅበሩ የኮምዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ መስፍን ደረጀ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
ታጣቂዎቹ ተሽከርካሪዎቹን “ከታለመለት ዓላማ ውጭ እየተጠቀሙ ነው፤” ሲሉም የቢሮ ኃላፊው አመልክተዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም