በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩክሬኑ ጦርነት የዓለም ኢኮኖሚን ዕድገት ዝግ እንደሚያደርግ አይኤምኤፍ ተነበየ


ፎቶ ፋይል፦ የተለያዩ ሀገሮች የገንዘብ ኖቶች ሆንግ ኮንግ
ፎቶ ፋይል፦ የተለያዩ ሀገሮች የገንዘብ ኖቶች ሆንግ ኮንግ

ሩሲያ ዩክሬን ላይ ደረሰችው ወረራ የዓለም ኢኮኖሚ ዕድገት ዝግ እንደሚያደርገው ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት አይኤምኤፍ ዛሬ ማክሰኞ ባወጣው ሪፖርት ገለፀ።

የዓለም ምጣኔ ሀብት እአአ ባለፈው 2021 በስድስት ነጥብ አንድ ከመቶ ማደጉን ያስታወሰው የዓለም አቀፍ ገንዘብ ድርጅቱ ዘንድሮ ግን ዕድገት የሚኖረው በሦስት ነጥብ ስድስት ከመቶ ብቻ እንደሚሆን ተንብዮል።

ጦርነቱ በምጣኔ ሀብት ላይ ያሳደረው አንድምታ ራቅ እያለም አድማሱንም እያሰፋ ነው ያለው የዓለም የገንዘብ ተቋሙ ብሏል።

የውጭ ንግድ የመሳሰሉ እንቅስቃሴዎችን በማስተጓጎል እንዲሁም የነዳጅ እና የምግብ ዋጋ ንረት በማስከተል የዓለም ኢኮኖሚ ወደ አሉታዊ አቅጣጫ እንዲያመራ አድርጓል ሲልም አመልክቷል።

ዋናው የአይኤምኤፍ ኢኮኖሚስት ፒየር ኦልቪዬ ጉሪንቻስ በጻፉት የዓለም ኢኮኖሚ ትንበያ ሪፖርቱ መግቢያ "በዓለም አቀፉ ወረርሽኝ ምክንያት ተንኮታኩቶ የነበረው የዓለም ኢኮኖሚ ጠንከር ብሎ ሊያንሰራራ ተቃርቦ ነበር።

ጦርነቱ መጣና በቅርብ ጊዚያት የተገኙ አብዛኞቹን ስኬቶች ጠራርጎ የሚያጠፋ ሁኔታ ፈጠረ።" ብለዋል።

የሩሲያ ምጣኔ ሀብት በዚህ ዓመት በ8 ነጥብ አምስት ከመቶ የዩክሬይን ደግሞ በሰላሳ አምስት ከመቶ እንደሚያሽቆለቁል የገንዘብ ድርጅቱ ተንብዮል።

XS
SM
MD
LG