በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የመንግሥታት ዕዳ በእጅጉ እያሻቀበ ነው” አይኤምኤፍ


የዐለም መንግሥታት ያለባቸው ዕዳ የኮቪድ 19 ወረረሽኝ በከፋበት ጊዜ ከነበረው ወዲህ በከፍተኛ ደረጃ እያሻቀበ ነው ሲል ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) አስጠነቀቀ፡፡

በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ያሻቅባል ተብሎ ከሚጠበቀው ዕዳ እጅግ የሚበዛው የሚጠበቀው በቻይና እና በዩናይትድ ስቴትስ እንደሚሆን የአይኤም ኤፍ የሀገሮች ገቢዎች ክፍል ኃላፊ ቪቶር ጋስፐር ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ተናግረዋል፡፡

ኃላፊው ይህን ያሉት ትናንት ረቡዕ ይፋ የተደረገው አይኤምኤፍ ሪፖርቱን ከማውጣቱ በፊት መሆኑ ተነግሯል፡፡

“የዚህ የአውሮፓውያኑ 2023 ዓመተ የመንግሥታት ዕዳ ከኮቪድ ወረርሽኙ በፊት ይደርሳል ተብሎ ከተጠበቀው አልፏል” ብለዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ዕዳ ከአጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርቱ ድምሩ ጋር ሲነጻጸር እኤአ በ2027፣ ከወረረሽኙ በፊት ከነበረበት የበለጠ እንደሚሆንም ኃላፊው አመልክተዋል፡፡

የቻይና ዕዳ ከአጠቃላይ ምርት ድምር ጋር ሲነጻጸር በየዓመቱ እየጨመረ እንደሚሄድም ጋስፐር ገልጸዋል፡፡

እንደ አይኤምኤፍ ግምት እኤአ በ2028 የቻይና ዕዳ ጫና ከወረረሽኙ በፊት ከነበረው በእጥፍ ይልቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከቻይናና ዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ያሉ የሌሎች ጥቂት አገሮች የዕዳ ጫና በዓመቱ አጋማሽ የተሻለ ገጽታ መያዙም ተጠቅሷል፡፡

ከ60 ከመቶ በላይ የሚሆኑ አገሮች ዕዳ ከአጠቃላይ ምርት ድምር ጋር ሲነጻጸር በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት እየቀነሰ እንደሚመጣ ጋስፓር ተናግረዋል፡፡

እየጨመረ የመጣውን ዓለም አቀፍ እዳ ለመቀነስ አይኤምኤፍ “ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ” እያወጣ መሆኑንም ኃላፊ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ጥብቅ የፋይናንስ ቁጥጥር “ከፍተኛ የወለድ መጠን ጭማሪ ሳይኖር” የገንዘብ ፖሊሲው የዋጋ ግሽበት እንዲቀንስ ያደርገዋል በህብረተሰቡም ውስጥ እንዲሁ የተመጣጠነ የዋጋ ክፍፍል እንዲኖር ይፈቅዳል” ሲሉ የአይኤምኤፍ የመንግሥታት ገቢ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊው ቪቶር ጋስፐር ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG