በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አይ ኤም ኤፍ የብድር ጥያቄዋን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ጋራ ተወያየ


የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት(IMF)
የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት(IMF)

የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት(አይ ኤም ኤፍ) ሠራተኞች ከእ.ኤ.አ መስከረም 25 እስከ ጥቅምት 3፣ 2023 ዓ/ም ድረስ ኢትዮጵያን መጎብኘታቸውን ድርጅቱ ትናንት ሐሙስ አስታወቋል፡፡

ድርጅቱ እንዳስታወቀው ምሥራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር የእርስበርስ ጦርነቱን ለማስቆም የተኩስ አቁም ስምምነት ከተደረሰ አንድ ዓመት ያህል ጊዜ በኋላ አሁንም ርዳታ መፈለጓን ቀጥላለች፡፡

"በተጠየቀው ፕሮግራም የማሻሻያ ማዕቀፎች ላይ ስምምነት ላይ ለመድረስ በሚቀጥሉት ሳምንታት ውይይቶች ይቀጥላሉ" ሲሉ የአይኤምኤፍ የኢትዮጵያ ሃላፊ አልቫሮ ፒሪስ ተናግረዋል።

"በተለይም ከመንግሥት የገንዘብ ወጪ እና ገቢ አያያዝና አጠቃቀም (ፊስካል) እንዲሁም የገንዘብ ወጪ ማጠናከሪያን ጨምሮ የዋጋ ንረትን ለማርገብ እና ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት ጠቃሚ እርምጃዎች " ናቸው ሲል የድርጅቱ መግለጫ አስታውቋል፡፡

በአፍሪካ በሕዝብ ብዛት ሁለተኛ የሆነችው ሀገር፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ሀገራት የመንግሥት እዳ በሚያዋቅረው በቡድን 20 የጋራ ማዕቀፍ ሥር በ እ.ኤ.አ. በ2021 መጀመሪያ ላይ ሰፊ የዕዳ ክለሳ መጠየቋ ተጠቅሷል፡፡

ይሁን እንጂ እ.ኤ.አ. ኅዳር 2020 የተቀሰቀሰው የሁለት ዓመቱ የእርስ በርስ ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት በመቅጠፉና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩትን ደግሞ በማፈናቀሉ ጉዳዩ ተወሳስቦ እንደነበር የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG