በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አይኤምኤፍ የባለሞያዎች ቡድን ወደ አዲስ አበባ ሊልክ ነው


ፎቶ ፋይል፡ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት/አይኤምኤፍ/ ዋና መሥሪያ ቤት ዋሺንግተን ዲሲ
ፎቶ ፋይል፡ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት/አይኤምኤፍ/ ዋና መሥሪያ ቤት ዋሺንግተን ዲሲ

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት/አይኤምኤፍ/ ኢትዮጵያ እያቀረበች ላለችው የብድር ጥያቄ ምላሽ በመጭዎቹ ሳምንታት አንድ የልዑካን ቡድን ወደ አዲስ አበባ እንደሚልክ የድርጅቱ ቃል አቀባይ ጁሊ ኮዛክ ትላንት አስታወቁ።

ልዑኩ ባለፈው የጥቅምት ወር በተመሳሳይ ወደ አዲስ አበባ ያደረገውን ጉዞ ተከትሎ ድርጅቱ “ባለሥልጣናቱ ያቀረቡትን የኢኮኖሚ መርሃ ግብር መደገፍ በሚችልበት መንገድ ዙሪያ ሁነኛ እመርታ ታይቷል" ያሉት ኮዛክ ቡድናቸው ወደ ኢትዮጵያ የሚያቀናበትን ትክክለኛ ቀን ግን አላሳወቁም።

አያይዘውውም የብድር ገንዘቡ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ በግጭቶች ለደረሰው ውድመት የመልሶ ግንባታ እና በሃገሪቱ የሚታየው ከፍተኛ የዋጋ ንረት ያስከተለውን ሁኔታ ለማርገብ፤ እንዲሁም የሰብአዊ ፍላጎቶች ማሟላትን ጨምሮ ኢትዮጵያ የገጠሟትን ብርቱ ፈተናዎች ለመቅረፍ መሆኑን አመልክተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG