በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም ኢኮኖሚ ጥቂት እድገት ቢያሳይም ከከባዱ ችግር እንዳልወጣ አይኤምኤፍ ገለጸ


የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት(IMF)
የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት(IMF)

የዓለም ኢኮኖሚ፣ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና ከሩሲያው የዩክሬን ወረራ ጫና፣ ቀስ በቀስ እያገገመ ቢኾንም፣ “ካለበት ከፍተኛ ችግር ገና አልወጣም፤” ሲሉ፣ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት(IMF) ከፍተኛ የምጣኔ ሀብት ባለሞያ ፒየር ኦሊቨየር ጎሪንቻስ ተናገሩ፡፡

ባለሞያው ግምገማቸውን የሰጡት፣ አይኤምኤፍ፣ እ.ኤ.አ. በ2023 እና በ2024፣ የዓለም ኢኮኖሚ እድገት ወደ ሦስት ከመቶ እንደሚቀንስና ይህም፣ እ.ኤ.አ. በ2022 ከነበረው፣ በ3ነጥብ5 ከመቶ ዝቅ እንደሚል በተነበየበት ወቅት ነው፡፡

የቅርብ ጊዜ ትንበያው፣ ከሦስት ከመቶ በታች እድገት ያስመዘገበው የዓለም ኢኮኖሚ፣ የረኀብ እና ድህነትን አደጋ እንደሚያስከትል፣ የድርጅቱ አመራር፣ በሚያዝያ ወር ከተነበየው፣ በ0ነጥብ2 ከመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

የምጣኔ ሀብቱ እድገት መጠነኛ መሻሻል ቢያሳይም፣ ዓለም አቀፍ ምጣኔው “በታሪካዊ መለኪያዎች ደካማ እንደኾነ ቀጥሏል፤” ሲል፣ የአይኤምኤፍ ዘገባ አመልክቷል፡፡

ባለሞያው ጎሪንቻስ እንዳስጠነቀቁት፣ አንዳንድ አሉታዊ ስጋቶች ቢሻሻሉም፣ ሚዛኑ፣ አሁንም ወደ ታች እንዳጋደለ ይቆያል፤ ብለዋል፡፡

ዓለም አቀፉ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ፣ እመርታዊ እድገቱን ያጣ እንደኾነ የሚጠቁሙ ምልክቶች እየጨመሩ በመኾናቸው፣ ድሉን ለማክበር ጊዜው ገና ነው፤ ሲሉም ባለሞያው አስጠንቅቀዋል፡፡

ባለሞያው አክለውም፣ ሩሲያ በቅርቡ፣ የዩክሬን እህል ለዓለም ገበያ እንዲቀርብ ከሚያስችለው ከ “ጥቁር ባህር የእህል ስምምነት” መውጣቷ፣ የምግብ ዋጋን ከፍ ሊያደርገው እንደሚችል ያመላክታል፤ ብለዋል፡፡

“አሁን የት ላይ እንደምናርፍ እየገመገምን ነው፡፡ የ10 እና የ15 ከመቶ የእህል ዋጋ ጭማሪ ላይ ከደረስን፣ ያ ምክንያታዊ ግምት እንደኾነ እናስባለን፤” ብለዋል ጎሪንቻስ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG