በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የመካከለኛው ምስራቅና የሰሜን አፍሪካ ኢኮኖሚ ጠንካራ ነበር” ፟ አይኤምኤፍ


ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) የመካከለኛው ምስራቅ እና የሰሜን አፍሪካ ሃገሮች ምጣኔ ሀብት እንደ አውሮፓውያኑ የዘመን አቆጣጠር በ2022 ጠንካራ እንደነበሩ ገልጾ፣ ሆኖም ባለ ሁለት አሃዙ የዋጋ ግሽበት በሚቀጥለው ዓመት በቀጠናው የሚኖረው እድገት አዝጋሚ እንዲሆን ያደርገዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስታውቋል፡፡

አይኤምኤፍ ዛሬ ሰኞ ባወጣው መግለጫ በቀጠናው ያሉት አገሮች አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት እንደ አውሮፓውያኑ የዘመን አቆጣጠር በ2022 በ5ከመቶ እንደሚያድግ ተንብይዋል፡፡

በዩክሬኑ ጦርነት የተነሳ አንዳንድ የአውሮፓ አገሮች የሚገዙትን የነዳጅ ዘይት ከሩሲያ በመግዛት ትተው ወደ ሌላ አገር በማዛወራቸው በተፈጠረ የንግድ ለውጥ ተጠቃሚ የሆኑ የነዳጅ ዘይት አምራች አገሮች የአገር ውስጥ ምርት እድገት ደግሞ 5.2 ከመቶ መሆኑን አይኤምኤፍ አስታውቋል፡፡

ይሁን እንጂ በከፍተኛ የምግብና የሸቀጥ ዋጋ ሳቢያ፣ እንደ አውሮፓውያኑ የዘመን አቆጣጠር በ2023 ለሦስት ተከታታይ ዓመታት የዋጋ ግሽበቱ በእጥፍ ያድጋል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን የቀጠናውንም እድገት አዝጋሚ እንዲሆን ያደርገዋል ሲል አይኤምኤፍ አስታውቋል፡፡

በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ዘይት ላኪ አገሮች የሚፈሰው ተጨማሪ ገቢ እና የፋይናንስ ክምችት መጠን ከአንድ ትሪሊዮን ዶላር በላይ እንደሚሆን ይጠበቃል ሲልም ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ተንብይዋል፡፡

XS
SM
MD
LG