በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከሰሃራ በታች ያሉ ሀገራት በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ቦርድ ተጨማሪ መቀመጫ ያገኛሉ


ፎቶ ፋይል፦ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅቱ ሓላፊ ክርስታሊና ጆርጂቫ
ፎቶ ፋይል፦ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅቱ ሓላፊ ክርስታሊና ጆርጂቫ

ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራት፣ በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ቦርድ ውስጥ፣ ሦስተኛ ተጨማሪ ወንበር ያገኛሉ፡፡

ሀገራቱ በሚያገኙት ተጨማሪ መቀመጫ፣ “ጠንከር ያለ ድምፅ ይኖራቸዋል፤” ሲሉ፣ የድርጅቱ ሓላፊ ክርስታሊና ጆርጂቫ፣ ለአሶሺዬትድ ፕረስ ዜና ወኪል ተናግረዋል።

ጠንከር ያለ ድምፅ ይኖራቸዋል፤”

ሓላፊዋ ዜናውን ያበሠሩት፣ ከ50 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ በቀጣዩ ሳምንት በማራከሽ - ሞሮኮ የሚካሔደውን የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጀት (IMF) እና የዓለም ባንክ ስብሰባ አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ነው።

በክርስታሊና ጆርጂቫ የሚመራው የገንዘብ ድርጅቱ ቦርድ፣ የዋሽንግተን ዲሲ ዋና መሥሪያ ቤቱን የዕለት ተዕለት ሥራ የሚያንቀሳቅስ ሲኾን፣ 24 ዲሬክተሮች አሉት፡፡

በዓለም ትልቁ ኢኮኖሚ የኾነችው አሜሪካ፣ በቦርዱ ውስጥ የድምፅ ብልጫ ሲኖራት፤ ጃፓን፣ ቻይና እና ምዕራብ አውሮፓ እንደቅደም ተከተላቸው ይቀመጣሉ።

ከሰሃራ በታች ላሉ ሀገራት የሚሰጠው ተጨማሪ ወንበር፣ ከመጪው ሰኞ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በማራከሽ ከተማ በሚደረገው ጉባኤ ላይ ይፋ እንደሚኾን ይጠበቃል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG