በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም ምጣኔ ኃብት ማሽቆልቆሉን ቀጥሏል


የዓለም ኢኮኖሚ እድገት እጅግ አዝጋሚ እየሆነ መምጣቱና ፈጥኖ የማገገሙ ሁኔታም የጨለመ መሆኑን ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይኤምኤፍ ትናንት ማክሰኞ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

አይኤምኤፍ ባለፈው ዓመት በመላው ዓለም የነበረው የ6.1 ከመቶ እድገት በዚህ ዓመት ወደ 3.2 ከመቶ ዝቅ እንደሚል ገምቷል።

እኤአ በ2021 ታይቶ የነበረው ጊዚያዊ እድገት በ2022 በተከሰቱ ሁኔታዎች መልሶ መጨለሙን ዓለምአቀፉ የገንዘብ ተቋም ገልጿል።

በዚህ በሁለተኛው የ2022 ሩብ ዓመት በቻይናና በሩሲያ የታየው ማሽቆልቆል እንዲሁም በዩናይትድ ስቴትስ የሸማች ወጭ ክተጠበቀው በታች መሆን ለዓለምአቀፍ ምርት መቀነስ ምክንያት መሆኑን ተቋሙ አመልክቷል።

የዓለም ኢኮኖሚ በተለያዩ ቀውሶች የተመታ መሆኑን የገለጸው አይ ኤም ኤፍ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ የተጎዳው ኢኮኖሚ በተለይም በዩናይትድ ስቴትስና በአውሮፓ የታየው ግሽበት ጥብቅ የሆነ የፋይናንስ ሁኔታን መፍጠሩን አስታውቋል፡፡

በቻይና የኮቪድ ወረረሽኝና የተቋማት መዘጋጋት ከተጠበቀው በላይ አዝጋሚ ሁኔታ መፍጠሩ፣ በዚያ ላይ የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት ሲጨመር አሉታዊ ተጽእኖዎቹ ወደሌሎችም እንዲስፋፉ ማድረጉንም ተቋሙ አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG