በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍሪካ፣ እሥያና አረቦች ማኅበራዊ ጥበቃ የላቸውም


ከዓለም ሕዝብ ከግማሽ የሚበልጠው ማኅበራዊ ጥበቃ የማያገኝና ማለቂያ በሌለው የድኅነት ቀለበት ውስጥ የሚኖር ነው ሲል ዓለምአቀፉ የሥራ ድርጅት አስታወቀ።

ከዓለም ሕዝብ ከግማሽ የሚበልጠው ማኅበራዊ ጥበቃ የማያገኝና ማለቂያ በሌለው የድኅነት ቀለበት ውስጥ የሚኖር ነው ሲል ዓለምአቀፉ የሥራ ድርጅት አስታወቀ።

ድርጅቱ ይህንን ያስታወቀው ትናንት ዋና መሥሪያ ቤቱ የሚገኝባት ጄኔቫ ላይ ባወጣው የዓለም የማኅበራዊ ጥበቃ ሪፖርቱ ላይ ነው።

በዘንድሮው የዓለም ሕዝብ ብዛት ግምት መሠረት ወደ ስምንት ቢሊዮን ከሚጠጋው ሰው 55 ከመቶ ወይም አራት ቢሊዮኑ አንዳችም ዓይነት ማኅበራዊ ጥበቃ የለውም።

ይህንን ሁኔታ ‘ጨርሶ ተቀባይነት ሊኖረው የማይችል’ ሲሉ የዓለም የሥራ ድርጅት - አይኤልኦ ዋና ዳይሬክተር ጋይ ራይደር ገልፀውታል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

አፍሪካ፣ እሥያና አረቦች ማኅበራዊ ጥበቃ የላቸውም
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:48 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG