መቀሌ —
የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ከምሥራቅ አፍሪካ የጋራ ልማት ትብብር ተቋም (IGAD) በተሰጠው ድጋፍ ከአምስት አገሮች የተውጣጡ ዘጠኝ ተማሪዎችን ትላንት ሲያስመርቅ በውኃና በደን ጥበቃ መርኃ ግብር ሁለተኛ ዲግሪ ሰጥቷል፡፡
ተመራቂዎቹ የኢትዮጵያ፣ የጂቡቲ፣ የሶማሊያ፣ የሱዳንና የደቡብ ሱዳን ዜጎች እንደሆኑ ታውቋል።
በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የመሬትና የውኃ ልማት ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶክተር እያሱ ያዘው የትምህርቱ ዓላማ በአፍሪካ ቀንድ ያለውን የውኃ እጥረትና የደን ውድመት ችግር በጋራ የሚፈቱ ባለሙያዎችን ለማሠማራት እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።