በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢጋድ አባል አገሮችን ውሳኔ አስመልክቶ የተካሄደ ግምገማ


ስድስት የምሥራቅ አፍሪቃ ሀገሮች መሪዎች ባለፈው እሁድ በጠሩት ስብሰባ፥ 2 ሺህ ወታደሮችን ወደ ሱማልያ ባስቸኳይ ለመላክ ተስማምተዋል። የሽግግሩ መንግሥት ጠላቶቹን ለማሸነፍ እንዲያግዘውም፥ ተጨማሪ በርካታ ቁጥር ያላቸው ወታደሮችን በመላ አገሪቱ ለመመደብም ቃል ገብተዋል።

ይህን የኢጋድ አባል አገሮች ውሳኔ በጽኑ የሚቃወመው ነውጠኛው የአል ሻባብ ቡድን፥ እሁድ ዕለት ዑጋንዳ ውስጥ ለደረሱትና ከሰባ በላይ ሲቪሎች ለተገደሉበት ጥንድ የቦንብ ጥቃት ኃላፊነቱን ወስዷል።

ይህን መሰሉ ትላንት በዑጋንዳ ላይ የደረሰ አሰቃቂ የቦምብ ጥቃት በሌሎች ወታደሮቻቸውን ወደ ሱማልያ ለመላክ በወሰኑ አገሮችም ላይ ሊደርስ እንደሚችል ያሰጋል።

ለማንኛውም ከዚህ ቀደም የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት የሱማልያ ተጐራባች አገሮች ወታደሮቻቸውን ወደ ሱማልያ እንዳይልኩ ከደረሰበት ውሳኔ አንፃር ያሁኑ ኢጋድ ያቀረበው ሃሳብ እንዴት ይታያል ?

ሰሎሞን ክፍሌ የቀድሞውን በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ዴቭድ ሺንን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል።

ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG