በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“በግጭት ወቅት በጤና ተቋማትና ህሙማ ላይ የሚደርሰው ጥቃት ተባብሷል” - አይሲአርሲ


የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታ ምክር ቤት በግጭት ቀጣናዎች ያሉ የጤና ሰራተኞች የደህንነት ጥበቃ እንዲደረግላቸው እና ጥቃት ፈጻሚዎችም በተጠያቂነት እንዲያዙ ከአምስት ዓመታት በፊት የመጀመሪያውን ውሳኔ ማሳለፉ የሚያታወስ ሲሆን ባለፉት ዓመታት ውስጥ በጤና ሰራተኞች፣ በቁስለኞች እና በህመምተኞች ላይ የሚፈጸመው ግድያ እና አካላዊ ጥቃት እንደቀጠለ ገልጿል።

የቀይ መስቀል ዓለም አቀፍ ኮሚቴ ዛሬ ሰኞ ባወጣው መግለጫ ውሳኔው ከተላለፈ ወዲህ በሀገሮች የጤና ስርዓቶች ላይ በተፈጸሙ በሽዎች የተቆጠሩ ጥቃቶች የጤና ሰራተኞች እና ታካሚዎቻቸው ለስቃይ እንደተዳረጉ አስታውቋል። አያይዞም መግለጫው የህክምና ተቋማት፣ እና የህሙማን ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎች ላይ ዘረፋና ውድመት ተፈጽሟል ብሏል።

የክትባት መርሃ ግብሮችን ጨምሮ የህዝብ ጤና አገልግሎቶች ላይ ጥቃት መድረሱንም አመልክቷል።

እአአ ከ2016 እስከ 2020 በነበሩት ዓመታት በሠላሳ ሦስት ሃገሮች ውስጥ በአማካይ 3780 ጥቃቶች እንደደረሱ የገለጸው ቀይ መስቀል ከዚህ ውስጥ ሁለት ሦስተኛው የደረሰው አፍሪካ፥ እና መካከለኛው ምስራቅ ውስጥ እንደሆነ አብራርቷል።

ኮቪድ-19 ጥቃቶቹን ጋብ እናዳላደረገ የገለጸው ቀይ መስቀል ባለፈው ዓመት ከየካቲት እስከ ሃምሌ በነበሩት ወራት ውስጥ በጤና ሰራተኞች፣ በታካሚዎች እና በጸረ በኮቪድ-19 ተቋማት ላይ 611 የኃይል ጥቃቶች መፈጸማቸውን እና ይህም ለወትሮው በአማካይ ከሚደርሰው በሃምሳ ከመቶ የበለጠ መሆኑ ጠቅሷል።

በአይሲአርሲ በግጭት እና በአጣዳፊ ሁኔታዎች ወቅት ደህንነቱ የተጠበቀ የጤና አገልግሎት ተደራሽ የጤና ጥበቃ እና ተያያዥ አደጋዎች መርሃ ግብር ሃላፊው ማሲዬዥ ፖልኮውስኪ በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። የጤና ሰራተኞችንና የታካሚዎች ደህንነትን ለማረጋገጥ በፖለቲካ መሪዎች ዘንድ ፈቃደኝነቱም ሆነ ቀውሶች እንደሚከሰቱ ገምቶ የመዘጋጀት ጉድለት እንዳለ አመልክተዋል።

XS
SM
MD
LG