በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰዎች ሕይወት እና ንብረት እንዲከበር ቀይ መስቀል ጥሪ አቀረበ


ውጥረት በበዛባቸው አካባቢዎች የሰዎች ሕይወት እና ንብረት እንዲከበር ቀይ መስቀል ጥሪ አቀረበ። ውጥረቶች እየተባባሱ በመጡበት በትግራይ እና አቅራቢያ ባሉ ሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች የሰዎች ሕይወት እና ንብረት እንዲከበር ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ጥሪ አቀረበ።

ቀይ መስቀል ዛሬ ባወጣው ማሳሰቢያ ያዘለ ጥሪው ግጭቶች ባሉባቸው በእነዚህ አካባቢዎች ጊዜው በጠበቀ ሁኔታ የሕክምና አገልግሎት እንዲያገኙ መደረግ እንዳለበትም አሳስቧል። በዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል የኢትዮጵያ ልዑክ ሃላፊ ኬቲ ሶረን፤ “የወታደራዊ እንቅስቃሴ እየጨመረ በመጣበት የሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል ሰዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀል፣ መሰረታዊ የሆኑ ፍላጎቶቻቸውን ማጣት እና አስቸኳይ የሰብዓዊ ረድኤት ሊያስፈልጋቸው ይችላል” የሚል ስጋት እንዳላቸው ገልፀዋል። አያይዘውም ፤ “በአንፃሩ የሰዎች ሕይወት እና ንብረቶች በአግባቡ እንዲጠበቁ ከተደረገ የተሰጋው ጉዳት ላይደርስ ይችላል” ብለዋል።

ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ በተመለከተ አዲስ አበባ እና መቀሌ ባለው ቢሮዎቻቸው አማካኝነት ክትትል እያደረጉ መሆኑ ኃላፊዋ ገልፀው፤ አስፈላጊውን የሰብዓዊ ረድኤት ርዳታ ለማድረግ በተጠንቀቅ ላይ መሆኑ አስታውቋል።

አስተያየቶችን ይዩ (1)

XS
SM
MD
LG