በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከአፍሪካ ሕዝብ አሥራ ሁለት ሚሊዮኑ ተፈናቅሏል


የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ፒተር ማውረር
የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ፒተር ማውረር

የአፍሪካ ሀገሮች የውስጥ ተፈናቃይ ዜጎቻቸውን በተመለከተ የተዘጋጀውን የካምፓላ ስምምነት ማፅደቅና ተግባራዊ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው የዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አስታውቀዋል፡፡

ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ የአፍሪካ ሀገሮች የውስጥ ተፈናቃይ ዜጎቻቸውን በተመለከተ የተዘጋጀውን የካምፓላ ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ ያግዛሉ ያላቸውን ምክረ ሀሳቦች ማቅረቡን ፕሬዚዳንቱ ፒተር ማውረር አፍሪካ ህብረት ውስጥ ተገኝተው በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች በተለይ ደግሞ በአፍሪካ በየሀገሮቻቸው ውስጥ መፈናቀል ከዓለም የከበዱ ወቅታዊ ፈተናዎች አንዱ መሆኑን የኮሚቴው ፕሬዚደንት ገልፀዋል፡፡

1.2 ቢሊዮን ህዝብ በሚኖርባት አፍሪካ 1.2 ሚሊዮን ሰው በያለበት ሀገር ተፈናቅሏል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ከአፍሪካ ሕዝብ አሥራ ሁለት ሚሊዮኑ ተፈናቅሏል
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:29 0:00

XS
SM
MD
LG