በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዓለምአቀፉ የቀይ መስቀል ኰሚቴ በኦጋዴን የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦቱን እንዳይቀጥል ተከለከለ።


ዓለምአቀፉ የቀይ መስቀል ኰሚቴ በኦጋዴን የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦቱን እንዳይቀጥል ተከለከለ።

የ ICRC ማለትም የዓለምአቀፉ ቀይ መስቀል ኰሚቴ ፕሬዘዳንት Jacob Kellenberger እንደገለጹት፥ ድርጅቱን ወደ ምሥራቅ ኦጋዴን አካባቢ እንደገና ለመመለስ በቀረበው ጥያቄ ላይ ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር የተደረጉ ንግግሮች ፍሬ አላፈሩም።

የኢትዮጵያ መንግሥት ባብዛኛው ሱማሌዎች ከሚኖሩበት ከኦጋዴን የዓለምአቀፉን ቀይ መስቀል የሰብዓዊ ዕርዳታ ሠራተኞች ከሕገ-ወጡ የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር ሽምቅ ተዋጊዎች ጋር ወግናችኋል ሲል በመክሰስ እንዲወጡ ያዘዘው እ አ ዘ አ ሐምሌ 2007 ዓ ም ነው። ICRC ግን ክሱን አይቀበልም።

የኢትዮጵያ መንግሥት በተጨማሪም፥ የጋዜጠኞችና ግብረሰናይ ድርጅቶችን የኦጋዴን እንቅስቃሴ ውሱን አድርጓል። በቅርቡ የወጣው የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሰብዓዊ መብቶች ሪፖርት ግን፥ የመንግሥቱ ደጋፊ ኃይሎች እጅግ አዋኪ እየሆኑ በመጡ በኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር ሽምቅ ተዋጊዎች ላይ የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ በሚያካሂዱበት አካባቢ የምግብና መድሃኒት አቅርቦቱን እንዳገደ ይጠቁማል።

በተለይ ባሁኑ ወቅት በሀገሪቱ ከባድ ድርቅ መከሰቱ ደግሞ የሰብዓዊ ድርጅቶችን ሥራ ይበልጥ ውስብስብ አድርጐታል።

የተባበሩት መንግሥታት የዓለም የምግብ ፕሮግራም WFP ደቡብና ደቡብ ምሥራቅ ኢትዮጵያን፥ እንዲሁም በከፊል ጐረቤት ሱማልያና ኬንያን ጨምሮ፥ በአፍሪቃ ቀንድ ሀገሮች በጠቅላላው ስምንት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ የሚጠጉ ሰዎች የምግብ ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል ብሏል።

ዝርዝሩን ያድምጡ

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG