በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በካርቱም አል ማይኮ ማዕከል 70 አሳዳጊ አልባ ሕፃናትን እንደሞቱ ዩኒሴፍ አስታወቀ


ሕፃናት በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም አውራ ጎዳና ላይ እየተጓዙ
ሕፃናት በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም አውራ ጎዳና ላይ እየተጓዙ

ከካርቱም አል ማይኮ ማዕከል 300 አሳዳጊ አልባ ሕፃናትን እንደታደገና ቢያንስ 70ዎቹ ግን እንደሞቱ ዩኒሴፍ አስታወቀ

በሱዳን ዋና ከተማ የሚገኘው፣ የተባበሩት መንግሥታት ዓለም አቀፍ የሕፃናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) እና አገር በቀሉ በጎ አድራጊ ድርጅት፣ ከሚያስተዳድረው አሳዳጊ አልባ የሕፃናት ማዕከል ለቆ መውጣቱን፣ ትላንት ረቡዕ አስታወቀ፡፡

ድርጅቱ ይህን ያስታወቀው፣ ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ፣ በአሳዳጊ አልባ የሕፃናት ማዕከል ውስጥ የነበሩ፣ ከ70 በላይ የሚደርሱ ጨቅላ እና አዳጊ ሕፃናት፣ በረኀብ እና በሕመም መሞታቸውን ተከትሎ ነው፡፡

ከወር በላይ ያስቆጠረው፣ የሱዳን ጦር እና የፈጥኖ ደራሽ ድጋፍ ሰጪ ኃይሎች ውጊያ በሚካሔድባት ካርቱም፣ አል ማይኮማ በተባለው የአሳዳጊ አልባ ሕፃናት ማዕከል ውስጥ፣ መውጫ አጥተው በአሠቃቂ ኹኔታ ከከረሙ ብዙ ሕፃናት መካከል፣ ቢያንስ 70 ጨቅላ እና አዳጊ ሕፃናት እንደሞቱ መነገሩ ይታወሳል፡፡

በአል ማይኮማ አሳዳጊ አልባ ሕፃናት ማዕከል ውስጥ ከነበሩት መካከል፣ ወደ 300 የሚደርሱ ሕፃናት፣ ለደኅንነታቸው አስተማማኝ ነው ወደ ተባለ ሌላ ቦታ መወሰዳቸውን፣ የተባበሩት መንግሥታት ዓለም አቀፍ የሕፃናት መርጃ ድርጅት(UNICEF) አስታውቋል፡፡

የሱዳን የማኅበራዊ ልማት እና ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ ሕፃናቱን በሓላፊነት ሲወስዱ፤ ዩኒሴፍ ደግሞ፥ የሕክምና፣ የምግብ እና የትምህርት እንቅስቃሴን ጨምሮ ሰብአዊ ድጋፍ ማድረጉን፣ አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

ሕፃናቱን ከአካባቢው በማስወጣት የረዳው፣ ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ፣ ከሕፃናቱ ጋራ 70 ተከባካቢዎች፣ ወደ ዐዲሱ ተቋም አብረው መዛወራቸውን አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG