በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አይሲሲ በሁለት የሩሲያ ጦር አዛዦች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ አወጣ


ዓለም አቀፉ የወንጀል ችሎት (አይሲሲ)የፍርድ ቤት ህንፃ በሄግ ፣ ኔዘርላንድስ እአአ ጥር 2019
ዓለም አቀፉ የወንጀል ችሎት (አይሲሲ)የፍርድ ቤት ህንፃ በሄግ ፣ ኔዘርላንድስ እአአ ጥር 2019

ዓለም አቀፉ የወንጀል ችሎት (አይሲሲ) በሁለት የሩሲያ ጦር አዛዦች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ ትናንት አውጥቷል።

ሰርጌይ ኮቢላሽ እና ቪክቶር ሶኮሎቭ በተባሉት የጦር አዛዦች ላይ የመያዣ ትዕዛዙ የወጣው፣ በዩክሬን በመካሄድ ላይ ባለው ጦርነት የጦር ወንጀል ሳይፈጽሙ አይቀርም በሚል ተጠርጥረው እንደሆነ በሄግ የሚገኘው ችሎት ገልጿል።

ከሁለት ዓመታት በፊት በእ.አ.አ ጥቅምት 2022 በሁለቱ መኮንኖች ትዕዛዝ በዩክሬን በሚገኙ የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማቶች ላይ ለተፈፀሙት የሚሳዬል ጥቃቶች ሓላፊነት እንደሚወስዱ በቂ ማስረጃ መኖሩን ችሎቱ አመልክቷል።

የሩሲያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ ዛሬ ረቡዕ በሰጡት መልስ፣ በሁለቱ የጦር መሪዎች ላይ የወጣውን የመያዣ ትዕዛዝ ሩሲያ ቦታ እንደማትሰጠውና እንደውም እንደ ትንኮሳ እንደምትቆጥረው አስታውቀዋል። “በሩሲያ በኩል ምንም ዓይነት ሕጋዊ ተፈፃሚነት የለውም” ሲሉም ተደምጠዋል።

በዩክሬን ከሚካሄደው ጦርነት ጋራ በተገናኘ ችሎቱ የመያዣ ትዕዛዝ ሲያወጣ ለሁለተኛ ግዜ ነው።

ችሎቱ ባለፈው መጋቢት በሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን እና በሕፃናት ኮሚሽነሯ ማሪያ ልቮቫ ቤሎቫ ላይ፣ በዩክሬን የሚገኙ ሕፃናት ታፍነው ከመወሰዳቸው ጋራ በተገናኘ የመያዣ ትዕዛዝ አውጥቶ ነበር።

“የመየዣ ትዕዛዞቹ ምዕራባውያን ሩሲያን ለማሳጣት የሚያደርጉት ሙከራ አካል ነው” ስትል ሞስኮ የፍርድ ቤቱን ሙከራ ታጣጥላለች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG