በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍ/ቤት በዩክሬን የሚፈጸሙ የጦር ወንጀሎችን ሊመረምር እንደሚችል አስታወቀ


በዩክሬን ኪየቭ ከተማ ላይ በደረሰው የሮኬት ጥቃትን ህንፃዎች ላይ ጉዳት ደርሷል፤ እአአ የካቲት 25/2022
በዩክሬን ኪየቭ ከተማ ላይ በደረሰው የሮኬት ጥቃትን ህንፃዎች ላይ ጉዳት ደርሷል፤ እአአ የካቲት 25/2022

የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ዐቃቢ ህግ ካሪም ካህን ሩሲያ ዩክሬንን መወረሯ እንዳሳሰባቸው ገልጸው በሀገሪቱ ውስጥ የሚፈጠሩ የጦር ወንጀሎችን ፍርድ ቤቱ ሊመረምር እንደሚችል አስታውቀዋል።

በዩክሬን ውስጥ እና ውጪ እየተፈጠረ ያለውን ሁሉ ነገር በእየጨመረ በመጣ ሥጋት እና አንክሮ እየተካተተሉት መሆኑን ያሳወቁት አቃቢ ህጉ፣ “የባላንጣነት ድርጊቶችን የሚፈጽሙ ሁሉንም አካላት፣ በዩክሬን ውስጥ የተፈጠረ የዘር ማጥፋት፣ በሰብዓዊነት ላይ የተቃጣ ወንጀል ወይንም የጦር ወንጀልን የመመርመር ሥልጣኑን መስሪያ ቤቴ ሊተገብር እንደሚችል ላስታውሳቸው እወዳለሁ” ብለዋል።

ሩሲያ ክሪሚያን በአውሮፓዊያኑ 2014 ዓመት ከግዛቷ በኃይል ከቀላቀለች፣ በአፍካሪ ሩሲያ እና የዩክሬን መንግሥት ኃይሎች መካከል ተከታታይ ውጊያ ከተደረገ በኃላ፣ ዩክሬን ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት በግዛቷ ላይ የሚፈጸሙ በሰብዓዊነት ላይ የተቃጡ ወንጀሎችን በተመለከተ ሥልጣን እንዲኖረው ከህዳር 2014 ዓመተምህረት ጀምሮ ተሰምታታለች።

በእአአ 2020 በነበረው ውጊያ ወቅት በምስራቅ ዩክሬን የጦር ወንጀሎች እና ሌሎች ወንጀሎች መፈጸማቸውን የሚሻምን ምክንያት እንዳለው አስታውቋል። የመጀመሪያ ደረጃ ምርመራው ቢጠናቀቀም ፣ ሙሉ ምርመራ እንዲከፈት የሚጠይቅ ሙሉ ጥያቄ ግን ለዳኞች አልቀረበም። ምርመራ ለመጀመር የዳኛ ፈቃድ ያስፈልጋል።

ሩሲያ የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት አባል አይደለችም፣ ይሁንና ፍርድ ቤቱ የወንጀል ፈጻሚዎች ዜግነት ከየትም ይሁን ከየት በዩክሬን ምድር የሚፈጸምን የጦር ወንጀል የመመርመር መብት አለው። ዘገባው የሮይተርስ ነው።

XS
SM
MD
LG