በዓለም አቀፉ የወንጀል ችሎት (አይ ሲ ሲ) ዋና አቃቤ ሕግ በእስራኤል እና ሐማስ መሪዎች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ ማውጣት እንደሚሹ ትናንት ሰኞ አስታውቀዋል።
የመያዣ ትዕዛዙ የእስራኤልን ጠቅላይ ሚኒስተር ቤንጃሚን ኔታንያሁ እና የሐማሱ መሪን ያህያ ሲንዋርን እንደሚጨምርና ይህም በጋዛ ጦርነት ላይ ለፈጸሙት ድርጊት መሆኑ ተመልክቷል።
አቃቤ ሕጉ ካሪም ካን በተጨማሪም በእስራኤሉ የመከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት እንዲሁም በሐማስ መሪዎች ሞሃመድ ዴይፍ እና ኢስማኤል ሃኒዬህ ላይም የመያዣ ትዕዛዝ ማውጣት እንደሚሹ አስታውቀዋል።
ኔታንያሁ እና ጋላንት የጦር ወንጀል እና በሰብዓዊነት ላይ ወንጀል በመፈጸማቸው “በወንጀል ተጠያቂ ይሆናሉ” ሲሉ ካን ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
የሐማስ መሪዎችም በተመሳሳይ የጦር ወንጀል እና በሰብዓዊነት ላይ ወንጀል በመፈጸማቸው፣ እንዲሁም ሰቆቃ፣ መድፈር፣ ጭካኔ የተሞላው አያያዝና አገታ በመፈጸም ተጠያቂ ይሆናሉ ብለዋል ዋና አቃቤ ሕጉ።
መድረክ / ፎረም