ዋሺንግተን ዲሲ —
የቡሩንዲ መንግሥት እአአ በሚያዝያ 2015 እና በጥቅምት 2017 መካከል ባለው ጊዜ በፖለቲካ ተቃዋሚዎቹ ላይ ፈፅሟል የተባለውን የጦር ወንጀል፣ ዓቃብያነህግ ምርመራችውን መጀመር እንደሚችሉ፣ ዓለማቀፉ የወንጀል ችሎት ዛሬ ሐሙስ አስታወቀ።
በሰብዓዊ ፍጡራን ላይ ደረሰ የተባለውን የወንጀል ምርመራ ለመቀጠል፣ በቂና ምክንያታዊ የሆኑ መሠረቶች እንዳሉ፣ ዳኞቹ ይፋ ባደረጉት መግለጫ አስታውቀዋል።
አስገድዶ መድፈር፣ ግድያ፣ ሰቆቃና እንግልት በቀላቀለው የወንጀል ድርጊት፣ ከ1ሺሕ በላይ ሰቆች ተገድለዋል፣ ወደ 40,0000 ያህሉ ደግሞ ተፈናቅለዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ